ፖለቲካ
ለዩክሬን ተዋጊዎችን ማሰለፍ “አደጋ አለው” ስትል አሜሪካ አስጠነቀቀች
ተዋጊዎችን ለዩክሬን መላክ የጦርነቱን አድማስ እንደሚያሰፋም ፔንታጎን አስታውቋል
ሩሲያ በበኩሏ ምዕራባዊያንን “እጎዳችዋለሁ” ስትል አስጠንቅቃለች
ለዩክሬን ተዋጊ ሰዎችን መላክ አደጋ ሊያስከትል ይችላል ሲል የአሜሪካው መከላከያ ሚኒስቴር ፔንታጎን አስታውቋል።
የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጆን ኪርቢይ በሰጡት መግለጫ፤ ለዩክሬን ተዋጊ ወታደሮችን መላክ የጦርነቱን አድማስ ያሰፋዋል ሲሉ አሳስበዋል።
ኬይቭን ለመደገፍ የተሻለው አማራጭ እንደ ፀረ ታንክ እና የአየር መከላከያ ያሉ የመከላከያ የጦር መሳሪያዎችን ማቅረብ መሆኑንም አስታውቀዋል።
ከምድር ወደ አየር የሚወነጨፉ የሚሳዔል መከላከያዎችን እና ሌሎችም ትጥቆችን ለዩክሬን ማቅረቡ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ቃላ አቀባዩ ጠይቀዋል።
ሌክሬን የሚደረጉ ሌሎች የጦር መሳሪያ ዝውውሮችም ቅድሚያ ሊሰጣቸው እንደሚገባም ፔንታጎን አስታውቋል።
ሩሲያ ከዚህ ቀደም በሰጠች መግለጫ፤ በዩክሬን የሚደረግ ማንኛውም አይነት ወታደራዊ ስምሪት መዘዙ እንደሚከፋ ማስጠንቀቋ ይታወሳል።
በትናትናው እለትም ምዕራባውያን እና ተባባሪዎችቻው የሆኑ የአውሮፓ እና ሌሎች ሀገራት እየጣሉባት ላለው ማዕቀብ ምለሽ ለመስጠጥ እየተዘጋጀት መሆኑን አስታውቃለች።
በዚህም ሩሲያ ምዕራባውያኑን እና ተባባሪዎቻውን “እጎዳችዋለሁ” ስትል ማስጠንቀቋ ተሰምቷል።