የሩሲያ ጦር የዩክሬኗን ከተማ እየከበበ መሆኑን የከተማዋ ባለስልጣናት ተናገሩ
በምዕራባውያን በምትደገፈው ዩክሬን እና ሩሲያ መካከል የተጀመረው ጦርነት 21 ወራትን አስቆጥሯል
የሩሲያ ኃይሎች የምስራቅ ዩክሬኗን አቪድቪካ ከተማ ለመያዝ ከሁሉም አቅጣጫ ጥቃት እያጠናከሩ መሆናቸውን የከተማዋ ከፍተኛ ባለስልጣናት ተናግረዋል
የሩሲያ ጦር የዩክሬኗን ከተማ እየከበበ መሆኑን ባለስልጣናት ተናገሩ።
ከሳምንታት ጦርነት በኋላ የሩሲያ ኃይሎች የምስራቅ ዩክሬኗን አቪድቪካ ከተማ ለመያዝ ከሁሉም አቅጣጫ ጥቃት እያጠናከሩ መሆናቸውን የከተማዋ ከፍተኛ ባለስልጣናት ተናግረዋል።
የሩሲያ ኃይሎች ከጥቅምት አጋማሽ ጀምሮ በመሬት እና በአየር በአቪድቪካ ላይ ጥቃት ሲያደርሱ መቆየታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ሩሲያ ወደ ከተማ እየቀረበች መሆኑን የአቪድቪካ ወታደራዊ አስተዳዳሪ ቪታሊ ባራባሽ ከመግለጻቸው ከሳምንት በፊት የዩክሬን ጦር የሩሲያን ጦር ግስጋዜ መግታቱን የሚገልጹ መረጃዎች ወጥተው ነበር።
ባራባሽ በአቪድቪካ ያለው ሁኔታ አስቸጋሪ መሆኑን እና ጦርነቱ እየጠነከረ መሄዱን ተናግረዋል።
የሩሲያ ኃይል ጥቃት ማድረስ ከጀመሩበት ከዶኔስክ ግንባር በተጨማሪ ሁለት ግንባር መክፈቱን የገለጹት ባራባሽ ጠላት ወደ ከተማዋ በሁለት አቅጣጫ መግባት ይፈልጋል ብለዋል።
በከተማዋ ለወራት በተደረገው ጦርነት አንድም ያልተነካ ህንጻ እንደሌለ የከተማዋ ባለስልጣናት ተናግረዋል።
አሁን በከተማዋ ከነበሩት 32ሺ ነዋሪዎች 1500 ብቻ ናቸው የቀሩት።
ከተማዋ በ2014 በሩሲያ በሚደገፉ ተገንጣዮች ለአጭር ጊዜ ተይዛ ነበር።
በምዕራባውያን በምትደገፈው ዩክሬን እና ሩሲያ መካከል የተጀመረው ጦርነት 21 ወራትን አስቆጥሯል።