ሩሲያ ከአጋሮቿ ጋር ወታደራዊ ልምምድ እንደምታካሄድ አስታወቀች
ከፓኪስታን፣ ከካዛኩስታን፣ ከአዘርቤጃን፣ ከህንድ እና ከደቡብ አፍሪካ የመጡ ተወካዮች በልምምዱ ላይ በታዛቢነት ይሳተፋሉ ተብሏል
ሩሲያ ከኢራን እና ከቻይና ጋር ወታደራዊ ልምምድ ልታደርግ መሆኑን አስታወቀች
ሩሲያ ከአጋሮቿ ኢራን እና ቻይና ጋር በኦማን ባህረ ሰላጤ ወታደራዊ ልምምድ ልታደርግ መሆኑን አስታወቀች።
ሩሲያ እንደገለጸችው ከቻይና እና ኢራን ጋር ለምታደርገው ወታደራዊ ልምምድ የጦር መርከቦቿ ኦማን ባህረሰላጤ እና አረቢያን ሲ ደርሰዋል።
የሩሲያ መንግስት መገናኛ ብዙሃን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴርን ጠቅሰው እንደዘገቡት "ማሪታይም ሴኩሪቲ ቤልት -2024" የተሰኘው ይህ ወታደራዊ ልምምድ የጦር መርከቦች እና የጦር ጀቶችን የሚያሳትፍ ነው።
"የተግባር ልምምዱ በኦማን ባህረ ሰላጤ ኤና በአረቢያን ሲ ይካሄዳል" ብሏል ሚኒስቴሩ።
ሚኒስቴሩ እንደገለጸው ከሆነ የልምምዱ ዋነኛ አላማ በማሪታይም ላይ የሚከናወኑ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎችን ደህንነት ለማስጠበቅ ነው።
በዚህ ልምምድ የሩሲያ ቡድን ከፓሲፊክ ፍሊት በመጣችው ቫርያግ ሚሳይል ተሸካሚ መርከብ እንደሚመራም ሚኒስቴሩ ጠቅሷል።
ከፓኪስታን፣ ከካዛኩስታን፣ ከአዘርቤጃን፣ ከህንድ እና ከደቡብ አፍሪካ የመጡ ተወካዮች በልምምዱ ላይ በታዛቢነት ይሳተፋሉ ተብሏል።
የምዕራቡን አለም ለመገዳደር በተቋቋመው ብሪክስ ውስጥ መስራች አባል የሆኑት ሩሲያ እና ቻይና በርካታ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ አድርገዋል።
ሩሲያም ሆነች ቻይና የምዕራባውያን ኢኮኖሚያዊ እና ወታደራዊ የበላይት አብቅቶ የዓለም ስርአት በእኩልነት ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ይፈልጋሉ።
በዓለም ኢክኖሚ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያለው ዶላርም ተፈላጊነቱ እንዲቀንስ ሀለቱ ሀገራት በአጋርነት እየሰሩ እንደሆነ ይነገራል።