ፖለቲካ
ሩሲያ ጄነራል አርማጌዶን በሚል ቅጽል ስም የሚታወቁቱን ሰርጌይ ስሮቪኪን አሰረች
ሞስኮ ጄነራል ሰርጌይ ስሮቪኪን ያሰረችው ከዋግነር ተዋጊ ቡድን ጋር ግንኙነት ነበራቸው በሚል ነው
በዩክሬን ዘመቻ እየመራ ያለው ጄነራል ስሮቪኪን ዋግነር አመጽ ለማካሄድ ማቀዱን ያውቁ ነበር ተብሏል
ሩሲያ ጄነራል አርማጌዶን በሚል ቅጽል ስም የሚታወቁቱን ጄነራል ሰርጌይ ስሮቪኪን በቁጥጥር ስር መዋሏ ተገለጸ።
ጄነራል ሰርጌይ ስሮቪኪን የታሰሩት ከዋግነር ቅጥረኛ ቡድን ወታደራዊ አመጽ ጋር በተያያዘ እንደሆነ ሞስኮ ታይምስ የሩሲያ ቋንቋ እና የሩሲያ ወታደራዊ ብሎገሮች ዘገባ ያመላክታል።
በዩክሬን ዘመቻ እየመሩ የሚገኙት የሩሲያ ጦር ምክትል አዛዥ ሰርጌይ ስሮቪኪን ፕሪጎዥን በሩሲያ ጦር ላይ አመጽ ለማካሄድ ማቀዱን መረጃው እንደነበራቸው ተነግሯል።
ጄነራል ስሮቪኪን በቁጥጥር ስር ሊውሉ የቻሉትም በዋግነር አመጽ ወቅት ከፕሪጎዥን ጎን በመቆማቸው ነው ብለዋል ምንጮች።
ጀነራል ሶሮቪኪን ባለፈው ጥቅምት ወር ነበር በዩክሬን ያለውን ዘመቻ እንዲመሩ የተመደቡት።
ነገርግን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ሰርጌ ሾጉ በዩክሬን ያለውን ዘመቻ የሚቆጣጠር ቫለሪይ ጌራሲሞቭን በመሾም፣ ሶሮቪኪን ምክትል እንዲሆኑ አድርገው ነበር።
ፕሪጎዥን ወደ አመጽ ከማምራቱ በፊት በዩክሬን ላለው የዘመቻ ውጤት ውድቀት በሰርጌ ሾጉ እና ጀነራል ጌራሲሞቭ ላይ ያነጣጠረ ወቅሳ ሲያቀርብ እንደነበር የሚታወስ ነው።