አንድ የሩሲያ ጀነራል የፕሪጎዥን እቅድ አስቀድመው ያውቁ እንደነበር የሚያመላክት ሪፖርት ወጣ
ፕሪጎዥን ለትንሽ ጊዜ አመጽ ካደረጉ በኋላ በተደረገው ድርድር ወደ ቤላሩስ እንዲሄዱ መደረጉ ይታወሳል
በፕሪጎዥን የአመጽ ተግባር ተቆጥተው የነበሩት ፑቲን ድርጊቱን የሀገር ክህደት ወንጀል ሲሉ መግለጻቸው ይታወሳል
አንድ ከፍተኛ የሩሲያ ጀነራል የዋግነር ታጣቂ ቡድን መሪ ፕሪጎዥን የአመጽ እቅድ አስቀድመው ያወቁ እንደነበር የሚገልጽ ሪፖርት መውጣቱን ሮይተርስ የኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣን ጠቅሶ ዘግቧል።
በዩክሬን ዘመቻ እየመራ ያለው የሩሲያ ጦር ምክትል አዛዥ ሰርጌይ ስሮቪኪን ፕሪጎዥን በሩሲያ ጦር ላይ አመጽ ለማካሄድ ማቀዱን መረጃው እንደነበራቸው ይላል ጋዜጣው።
ጋዜጣው ይህን የዘገበው የአሜሪካ የደህንነት ባለስለጣናትን ጠቅሶ ሲሆን ባለስልጣናቱ ጀነራሉ ለፕሪጎዥን ድጋፍ አድርገው እንደሆነ ለማወቅ እየጣሩ መሆናቸውንም ጠቅሷል።
ፕሪጎዥን ለትንሽ ጊዜ አመጽ ካደረጉ በኋላ በተደረገው ድርድር ወደ ቤላሩስ እንዲሄዱ መደረጉ ይታወሳል።
በፕሪጎዥን የአመጽ ተግባር ተቆጥተው የነበሩት ፑቲን ድርጊቱን የሀገር ክህደት ወንጀል ሲሉ መግለጻቸው ይታወሳል።
ዘገባው ሌሎች የሩሲያ ጀነራሎች ፕሪጎዥንን ሳይደግፉት አይቀሩም የሚል ጥርጣሪም አስቀምጧል።
ሮይተርስ ለስጉዳዩ የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴርን ጠይቆ መልስ አለማግኘቱን ገልጿል። በተመሳሳይ ሩሲያም መልስ በዚህ ጉዳይ መልስ አልሰጠችም ብሏል።
በቅጽል ስሙ ጀነራል አርማጌዲዮን እየተባለ የሚጠራው ጀነራል ሶሮቪኪን ባለፈው ጥቅምት ወር ነበር በዩክሬን ያለውን ዘመቻ እንዲመሩ የተመደቡት።
ነገርግን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ሾይጉ በዩክሬን ያለውን ዘመቻ የሚቆጣጠር ቫለሪይ ጌራሲሞቭን በመሾም፣ሶሮቪኪን ምክትል እንዲሆኑ አድርገው ነበር።
ፕሪጎዥን ወደ አመጽ ከማምራቱ በፊት በዩክሬን ላለው የዘመቻ ውጤት ውድቀት በጀነራል ሾይጉ እና ጀነራል ጌራሲሞቭ ላይ ያነጣጠረ ወቅሳ ሲያቀርብ ነበር።