ሩሲያ እና ኢራን በጋዛ ጦርነት ጉዳይ ምን አቋም ያዙ?
በእስራኤል ጥቃት የተገደሉ ሰዎች እስካሁን ከ13ሺ በላይ ማለፉን የጋዛ የጤና ባለስልጣናት ገልጸዋል
ሁለቱ ሀገራት በጋዛ ተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስ እና ንጹሃን እርዳታ እንዲያገኙ ጥሪ አቅርበዋል
ሩሲያ እና ኢራን በጋዛ ተኩስ እንዲቆም ያላቸውን አቋም አንጸባርቀዋል።
የሁለቱ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በትናንትናው እለት በሰጡት መግለጫ በጋዛ ተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስ እና ንጹሃን እርዳታ እንዲያገኙ ጥሪ አቅርበዋል።
ሩሲያ እንደገለጸችው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ሰርጌ ላብሮቭ በቴህራን ጥያቄ መሰረት ከኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆሴን አሚራብዶላሂያን ጋር ተነጋግረዋል።
ላቭሮብ "በንግግራቸው ወቅት ዋነኛ የትኩረት ነጥባቸው የፍልስጤም እና እስራኤል ግጭት ነበር" ብለዋል።
ከኢራን፣ ከሀማስ፣ ከዋናዋና የአረብ ሀገራት እንዲሁም ከፍልስጤም እና እስራኤል ጋር ግንኙነት ያላት ሩሲያ፣ በ1967 ስምምነት መሰረት የፍልስጤም መንግስት እንዳይመሰረት እንቅፋት ሆነዋል ያለቻቸውን አሜሪካን እና ምዕራባውያንን ትከሳለች።
ባለፈው ጥቅምት ወር ሀማስ የእስራኤልን ድንበር ጥሶ ያልተጠበቀ እና ከባድ ጥቃት ማድረሱን ተከትሎ እስራኤል በጋዛ የጥቃት ዘመቻ እያካሄደች ትገኛለች።
በእስራኤል ጥቃት የተገደሉ ሰዎች እስካሁን ከ13ሺ በላይ ማለፉን የጋዛ የጤና ባለስልጣናት ገልጸዋል።
በጋዛ የተኩስ አቁም እንዲደረግ አለምአቀፍ ጫና ቢደረግም፣ እስራኤል ጦርነቱን ጋብ ከማድረግ ውጭ ሀማስን ሳታጠፋ እንደማታቆም ደጋግማ አሳውቃለች።