በምስራቅ ዩክሬን አቭዲቭካ ከተማና ሌሎች ግንባሮች ውጊያዎች ተፋፍመው ቀጥለዋል
የእስኤልና የፍልስጤሙ ሃማስ ወደ ጦርነት ማራታቸውን ተከትሎ ባለፍነው ሳምንተ የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ጉይ ትኩረት ተነፍጎት ቆይቷል።
ዓለም ትኩረቱን መካከለኛው ምስራቅ ላይ ቢያደርግም በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል እየተካሄደ ያለው ጦርነት በምስራቅ ዩክሬን ተባበሶ መቀጠሉ ተነግሯል።
ጦርነት
በምስራቅ ዩክሬኗ አቭዲቭካ ከተማ ባለው ነግንባር ለተከታታይ አራተኛ ቀን ውጊያ መካሄዱን የቀጠለ ሲሆን፤ በግንባሩ ውጊያ የተጀመረው የሩሲያን ጥቃተ ተከትሎ እንደሆነ የከተማዋ የወታደራዊ አስተዳደር ኃላፊ ተናግረዋል።
ሩሲያ በትናንትናው እለት በጥቁር ባህር በምትገኘው ሶቺ ከተማ ላይ ሁለት የዩክሬን ድሮኖችም መትታ መጣሏን አስታውቃለች። ዩክሬን በሩሲያ ከተሞች ላይ የምታካሂዳቸው የድሮን ጥቃቶች ለወራት ተጠናክረው ቀጥለዋል።
በምሰራቅ ዩክሬን ዶንስክ ለወራት እየተካሄደ ያለው ከባድ ውጊያ ተጠናክሮ መቀጠሉን የዶኔክስ ክልል ተጠባባቂ አስተዳዳሪ አይሆር ሞሮዘዝ አስታውቀዋል።
ባለሱት 2ሰዓታት ሩሲያ በዶኔስክ በፈተጸመችው የአየር ድብደባም 22 ንጹሃን ዜጎች መሞታቸውንም ተጠባበቂ አስተዳዳሪው በቴሌግራም ገጻው አስታውቀዋል።
የክሬን ጦር ወታደሮቹ ከሩሲያ ወታደሮች ጋር ወደ 100 በሚጠጉ ግንባሮች እየተዋጉ ነው ያለ ሲሆን፤ ከግንባሮቹ ውስጥም ዶኔስክ፣ ሜሊቶፖል አካባቢ እና ዛፖሮዢያ ክልል እንደሚገኝበት አስታውቋል።
የጦር መሳሪያ
የአሜሪካ ባለስልጣናት ሰሜን ኮሪያ ለዩክሬን ጦርነት አገልግሎት ላይ የሚውል ከፍተኛ መጠን ያለው ወታደራዊ መሳሪያ ለሞስኮ አቅርባለች ሲሉ ከሰዋል።
የብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት ቃል አቀባይ ጆን ከርቢ ፒዮንግያንግ በቅርብ ሳምንታት ውስጥ "መሳሪያዎች እና ጥይቶች"ን የያዙ እስከ አንድ ሽህ ኮንቴይነሮችን አቅርባለች ብለዋል።
አሜሪካ እስራኤልን በመደገፍ ላይ ብትሆንም ለዩክሬን የምታደርገውን ጦር መሳሪያ እና ሌሎች ወታደራዊ ድጋች አጠናክራ እንደምትቀጥል አስታውቃለች።