ባማኮ የሚገነባው ይህ አዲስ የሚገነባው የወርቅ ማጣሪያ ሁሉንም ምርቶች ባንድ ላይ ለመቆጣጠር የሚያስችላት እንደሆነ ተገልጿል
ሩሲያ በማሊ የወርቅ ማጣሪያ ለመገንባት ተስማማች፡፡
ምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ማሊ ከሩሲያ ጋር ያላትን ወዳጅነት እና ትብብሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻሻለች መጥታለች፡፡
ከሶስት ዓመት በፊት በመፈንቅለ መንግስት ወደ ስልጣን የመጡት የሐገሪቱ ወታደራዊ መሪ ኮለኔል አስሚ ጎይታ ከምዕራባዊያን ጋር የነበሩ ስምምነቶችን ሰርዘዋል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ጨምሮ የፈረንሳይ እና ሌሎች ሀገራት ወታደሮችን ከሀገራቸው ያባረረችው ማሊ ከሩሲያ ጋር በወታደራዊ፣ ዲፕሎማሲ እና የኢኮኖሚ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ በመስራት ላይ ትገኛለች፡፡
አሁን ደግሞ በማሊ የሚመረቱ የወርቅ ምርቶችን መቆጣጠር የሚያስችል ማጣሪያ ለመገንባት ከሩሲያ ጋር መስማማቷን አስታውቃለች፡፡
በሀገሪቱ ዋና ከተማ ባማኮ ይገነባል የተባለው ይህ የወርቅ ማጣሪያ በዓመት 200 ቶን ወርቅ ማምረት የሚያስችል እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ሶማሊያ ለዓለም መሳቂያ አድርጎኛል ያለችውን የአትሌቲክስ ሀላፊ ከስራ አገደች
ግንባታው አራት ዓመት ይወስዳል የተባለው ይህ የወርቅ ማጣሪያ ማዕከል በምን ያህል ገንዘብ እንደሚገነባ ግን አልተገለጸም ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ማሊ በወርቅ ምርቷ የምትታወቅ ሲሆን ላለፉት ዓመታት ዋነኛ የንግድ አጋሯ ከነበረችው ፈረንሳይ ጋር ያላትን ትስስር አቋርጣለች፡፡
የማሊ ማዕድን ሚኒስትር አሉሴኒ ሳኑ እንዳሉት በሩሲያ የሚገነባው የወርቅ ማጣሪያ በሀገሪቱ የሚመረተውን አጠቃላይ የወርቅ መጠን ማወቅ እና ተገቢውን ግብር መሰብሰብ የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡