ሀገሪቱ በታጠቁ ቡድኖች የከፋ ጥቃት ሊደርስባት ይችላል ተብሎ ተሰግቷል
ተባበሩት መንግስታት ድርጅት በማሊ የሚገኘውን ሰላም አስከባሪ ሰራዊቱን ከታቀደው ጊዜ በፊት ማስወጣቱን አስታውቋል።
ተመድ ለእዚህ እርምጃው ምክንያቱ የሰላም አስከባሪዎች "ህይወት አደጋ ላይ በመውደቁ ነው" ብሏል።
ድርጅቱ የመጨረሻ ሰራዊቱ በቴሳሊት የሚገኘውን ካምፑን ለቆ ቅዳሜ ዕለት መውጣቱን ገልጿል።
በፈረንጆቹ 2023 ዓመት መጀመሪያ ላይ ሁሉም የተመድ እና የፈረንሳይ ወታደሮች ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ የሰጡት የማሊ ወታደራዊ መሪዎች፤ የቴሳሊት ካምፕ በቁጥጥራቸው ስር እንደሚገኝ ተናግረዋል።
የተመድ ሰላም አስከባሪ ኃይል ለመውጣት "ውጥረት የነገሰበት እና የተበላሸ የጸጥታ አውድ የሰራዊቱ ህይወት አደጋ ላይ ጥሏል" ሲል በማሊ የሚገኘው የተባበሩት መንግስታት የሰላም አስከባሪ ተልዕኮ (ሚኑስማ) በሰጠው መግለጫ ተናግሯል።
በማሊ የሚገኘው ጥቂት ዓለም አቀፍ ወታደሮች ባሉበት ሁኔታ ሀገሪቱ እስላማዊ ታጣቂዎችን ጨምሮ በታጠቁ ቡድኖች የከፋ ጥቃት ሊደርስባት ይችላል ተብሎ ተሰግቷል።