በሩሲያ በተካሄደ የከንቲባነት ምርጫ የከተማዋ የቀድሞ ከንቲባ በግል ሹፌሩ ሚስት ተበለጠ
ሩሲያ የከተሞቿን ከንቲባ በምርጫ ውጤት መሰረት እንዲመራ የሚፈቅድ ህግ ትከተላለች
የከንቲባ ምርጫው ውጤት ያልታሰበ እጩ ማሸነፉ አግራሞትን ፈጥሯል
በሩሲያ በተካሄደ የከንቲባነት ምርጫ የከተማዋ የቀድሞ ከንቲባ በግል ሹፌሩ ሚስት ተበለጠ፡፡
የቨግኒ ፒስቶቭ የሩሲያዋ በሬዞቭስኪ የተሰኘችውን ከተማ ለአራተኛ ጊዜ ከንቲባ ሆኖ ለመምራት በመወዳደር ላይ ነበር፡፡ በሀገሪቱ ህግ መሰረት ነዋሪዎች ከንቲባቸውን በቀጥታ ባይሆንም በወኪሎቻቸው አማካኝነት ይመርጣሉ፡፡
በዚህ ምርጫ ላይ ለዚች ከተማ ሁለት እጩዎች የከተማዋ ከንቲባ ሆኖ ለመስራት መዘገባሉ፡፡ ከዕጩ ከንቲባዎች ውስጥም የቨግኒ ፒስቶቭ እና የግል ሹፌሩ ሚስት ዩሊያ ማስላኮቫ ደግሞ ዋነኞቹ ናቸው፡፡
ምርጫውን እንዲያካሂዱ የተፈቀደላቸው የከተማዋ ነዋሪ ወኪሎች ተጨማሪ ዕጩዎች እንዲመዘገቡ ቢፈልጉም በስልጣን ባለው እና ለአራተኛ ጊዜ ከንቲባ ለመሆን ራሱን እጩ አድርጎ ያቀረበው ሰው ይህ እንዳይሆን የተለያዩ ጫዎችን አድርጓል ተብሏል፡፡
በዚህ የተበሳጩት መራጮችም ሁለተኛዋን እና ከንቲባውን በሹፌርነት እያገለገለ የሚገኘው ሰው ሚስት የሆነችው ዩሊያ ማስላኮቫን ከንቲባ አድርገው ይመርጣሉ፡፡
በምርጫው ውጤት በርካቶች ያልጠበቁት እና እጩዎችንም ያስደነገጠ ነው የተባለ ሲሆን በተለይም አሸንፈሻል የተባለችው ተወዳዳሪ ከፍተኛ ድንጋጤ ላይ ነች ተብሏል፡፡
የቀድሞው ከንቲባ ምርጫውን ለማሸነፍ እና ለይምሰል በምርጫው እንድታጅበው በሚል በውድድሩ እንድትካተት ያደረጋት ሴትም ስልጣኑን ልታሳጣው ደርሳለች፡፡
ምርጫውን አሸንፋለች የተባለችው እጩም ከምርጫው ልታገል ሞክራ ነበር የተባለ ሲሆን በቀድሞ አሰሪዋ በሚደርስባት ጫና ምክንያትም ከከንቲባነት ራሷን ልታገል እንደምትችል ኮሜርሳንት የተሰኘው የሩሲያ ሚዲያ ዘግቧል፡፡