ፖለቲካ
ሩሲያ የ'ጥቁር ባህር የእህል ስምምነት'ን ለማራዘም ፍላጎት እንደሌላት ገለጸች
በሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ተዘግቶ የነበረው የጥቁር ባህር ኮሪደር የተከፈተው በቱርክ እና በተመድ አደራዳሪነት ነበር
የሩሲያ የግብርና ሚኒስቴር ዲሜትሪ ፖትሩሼቭ እንደገለጹት ውሳኔው ፖለቲካዊ መሆኑን ገልጸዋል
ሩሲያ የ'ጥቁር ባህር የእህል ስምምነት'ን የማራዘም ፍላጎት እንደሌላት መግለጿን ሮይተርስ ዘግቧል።
የሩሲያ የግብርና ሚኒስቴር ዲሜትሪ ፖትሩሼቭ እንደገለጹት ውሳኔው ፖለቲካዊ መሆኑን ገልጸዋል።ሚኒስትሩ አክለውም ገዥዎች እስካሉ ድረስ ሩሲያ እህሏን ወደ ውጭ መላኳን ትቀጥላለች።
ሚኒስትሩ "ስምምነቱ ባይቀጥልም ወደ ውጭ የምንለከው የእህል መጠን አይቀንስም። የምንልከው የእህል መጠን በተወሰነ መልኩ ጨምሯል" ብለዋል።
ሩሲያ፣ ዩክሬን እህሏን ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ወደ ውጭ እንድትልክ ከሚያስችለው 'የጥቁር ባህር ስምምነት' የወጣችው ባለፈው ሐምሌ ወር ነበር።
ሩሲያ ከስምምነት የወጣችው ከዩክሬን የሚወጣው እህል ለድሃ ሀገራት እየደረሰ አይደለም በሚል ምክንያት ነበር።
ከዚህ በተጨማሪም ሩሲያ ስምምነቱ ለሩሲያ በሚጠቅም መልኩ አልተተገበረም የሚል ቅሬታም ማቅረቧ ይታወሳል።
በሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ተዘግቶ የነበረው የጥቁር ባህር ኮሪደር የተከፈተው በቱርክ እና በተመድ አደራዳሪነት ነበር።