የሉሃንስክ ክልል አስተዳዳሪ በአዞት ላይ የደረሰው ድብደባ በጣም ከባድ በመሆኑ ነዋሪዎች መቋቋም ከብዷቸዋል ብለዋል
ሩሲያ በሴቪዬሮዶኔትስክ ከተማ በሚገኝ የኬሚካል ፋብሪካ ውስጥ የመሸጉ የዩክሬን ሃይሎች መሳሪያ እንዲያወርዱ ጥሪ አቅርባለች፡፡ የሩሲያ የእጅ ስጡ ጥሪ በምስራቃዊ ዩክሬንን ለመቆጣጠር በሚደረገው ውጊያ ላይ ያላትን አቅም ለማሳየት ነው ተብሏል፡፡
ዩክሬን የምዕራባውያን ከባድ የጦር መሳሪያዎች ድጋፍ እንዲጨምር እየጠየቀች ነው፤ ሩሲያ ዶንባስን ነጻ አወጣለሁ በሚል አቅዷ ምክንያት አብዛኛውን ኃይሏን በምስራቃዊ ዶምባስ ግዛት ላይ ማከማቸቷን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የኔቶ የመከላከያ ሚኒስትሮች በብራሰልስ በሚያካሂደው ስብሰባ ላይ የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት በትኩረት ይነሳል ተብሏል፡፡
ዩክሬን በበኩሏ ከ500 የሚበልጡ ንፁሀን ዜጎች በአዞት የኬሚካል ፋብሪካ ውስጥ ከወታደሮች ጋር ተይዘው እንደሚገኙ ተናግራለች፡፡ በኬሚካል ፋብሪካ ውስጥ መሽጎ የነበረው ኃይል አብዛኛውን የሲቪዬሮዶኔትስክ ከተማ ወደ ፍርስራሽነት የቀየረውን የሩሲያ ጥቃት ሲከላከል ነበር፡፡
የሩሲያ ብሔራዊ መከላከያ አስተዳደር ማእከል ኃላፊ የሆኑት ሚካሂል ሚዚንሴቭ ለኢንተርፋክስ የዜና ወኪል እንደተናገሩት የዩክሬን ተዋጊዎቹ በሞስኮ ሰአትከቀኑ 08፡00 (05፡00 GMT) “ ትርጉም አልባ የሆነውን ውጊያ አቁመው መሳሪያቸውን መጣል አለባቸው፡፡
ሲቪሎች በሰብአዊነት ኮሪደር በኩል ይተላለፋሉ ብለዋል ሚዚንሴቭ፡፡
የአዞት ምሽግ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተዋጊዎች እና ሲቪሎች ከሩሲያ ጥይት የተጠለሉበትን በአዞቭስታል ብረት ፋብሪካ የተደረገውን ጦርነት ያስሳሻል፡፡በብረት ፋብሪካው ውስጥ የነበሩት በግንቦት ወር አጋማሽ ላይ እጃቸውን ሰጥተው ወደ ሩሲያ ተወስደው መታሰራቸው ይታወሳል፡፡
ሞስኮ በውክልና ስም ከምትጠራቸው ሁለት ምስራቃዊ ግዛቶች አንዱ የሆነው የሉሃንስክ የክልል አስተዳዳሪ ሰርሂ ጋይዳይ “በአዞት ላይ የደረሰው ድብደባ በጣም ከባድ ከመሆኑ የተነሳ ሰዎች በመጠለያው ውስጥ ሊሸከሙት አይችሉም፣ የስነ-ልቦና ሁኔታቸውም ችግር ላይ ነው” ብለዋል።
ከጦርነቱ በፊት ከ100,000 በላይ ሰዎች ይኖሩባት በነበረችው ሉሃንስክ ውስጥ በምትገኘው የሲየቪዬሮዶኔትስክ ከተማ ቤክሬን ትልቁ ጦርነት ተብሏል፡፡
የሩሲያ ጦር ወደ ከተማዋ የሚወስደውን የመጨረሻውን ድልድይ ካወደመ በኋላ ዩክሬን አሁንም ሰላማዊ ዜጎችን ለማስለቀቅ እየሞከረች ነው።
"ጠንክረን መቆየት አለብን… ጠላት ብዙ ኪሳራ ሲደርስበት ጥቃቱን ለመቀጠል ጥንካሬው ይቀንሳል" ሲል ዘለንስኪ ማክሰኞ ምሽት ባደረገው ንግግር።
የኔቶ ጦር ወደ ዩክሬን እየስፋፋ ነው፤ ይህም ለደህንነቴ ያሰጋኛል ያለችው ሩሲያ፤ በዩክሬን ላይ ልዩ ወደታደዊ ዘመቻ በመክፈት በሩሲያ የዶንባስ ግዛትን ለመቆጣጠር ጦርነት በማካሄድ ላይ ነች፡፡