ሩሲያ በወሰደችው የአጸፋ ምላሽ የዩኬ ዲፕሎማት ለቀው እንዲወጡ አዘዘች
የዩክሬን ጦርነት ከተጀረ በኋላ የምራባውያን ሀገራት እና የሩሲያ ጋር ያላቸውን ዲፕሎሲያዊ ግንኙነት ቀውስ ውስጥ ገብቷል።
ሩሲያ የዩኬን ወታደራዊ አታሼ ያባረረችው፣ እንግሊዝ አቻቸውን ካባረረች በኋላ በወሰደችው የአጸፋ ምላሽ ነው
ሩሲያ በወሰደችው የአጸፋ ምላሽ የዩናይትድ ኪንግደም(ዩኬ) ዲፕሎማት ለቀው እንዲወጡ አዘዘች።
ሩሲያ ወታደራዊ አታሼውን ያባረረችው፣ ዩኬ አቻቸውን ካባረረች በኋላ በወሰደችው የአጸፋ ምላሽ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውሳኔውን ለማሳወቅ በሀገሪቱ ያለውን ዩኬ ኢምባሲ ተወካይ መጥራቱን ገልጿል።
ዩኬ ከአንድ ሳምንት በፊት የሩሲያን ወታደራዊ አታሼ በይፋ ያልተገለጸ የስለላ ባለሙያ ነው በማለት እንዲወጣ ማዘዛ ይታወሳል።
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይህን የዩኬ ውሳኔ ፓለቲካዊ እና የሩሲያን ጥላቻ የሚያሳይ ነው፤ በሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ የማይጠገን ገዳት ያስከትላል ሲል ተቃውሞት ነበር።
የዩኬው ዲፕሎማት አድሪያን ጎሂል ሩሲያን ለቀው እንዲወጡ የአንድ ሳምንት ጊዜ ተሰጥቷቸዋል። ሞስኮ ይህ የችግሩ መቋጫ እንዳልሆነ እና የምትወስደውን ተጨማሪ የአጸፋ እርምጃ ለእንግሊዝ እንደምታሳውቅ ገልጻለች።
በሁለቱ ሀገራት መካከል የነበረው ግንኙነት ከዩክሬን ጦርነት በፊትም ችግር ውስጥ የነበረ ቢሆንም ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ የበለጠ ተባብሷል።
ዩኬ ከሩሲያ ጋር እየተዋጋች ላለችው ዩክሬን የጦር መሳሪያ በማቅረብ ወሳኝ ማና ተጫውታለች።
ባለፈው ሳምንት እንግሊዝ ከሩሲያ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ይዞታዎች የዲፕሎማታክ ስታተስ(ዲፕሎማሲያዊ እውቅና) እንደምታነሳ እና የሩሲያ ዲፕሎማቶች በእንግሊዝ በሚቆዩበት ጊዜ ላይ ገደብ እንደምትጥል ገልጻለች።
የዩክሬን ጦርነት ከተጀረ በኋላ የምራባውያን ሀገራት እና የሩሲያ ዲፕሎሲያዊ ግንኙነት ቀውስ ውስጥ ገብቷል።