ዘመቻው "እውነተኛ ወንድ" በሚል የተጀመረ ሲሆን በበጎ ፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ነው ተብሏል
ሩሲያ 400 ሺህ ወታደሮችን የመመልመል አዲስ ዘመቻ ጀመረች፡፡
የሩሲያ ጦር ዩክሬንን የሚዋጉ ወታደሮችን ለመመልመል ዘመቻ ጀምሯል።
በተንቀሳቃሽ ምስል የተጀመረው ዘመቻው ፍላጎት ያላቸውን ሰዎች "እውነተኛ ወንድ" መሆናቸውን በማሳየት እና የሲቪል ህይወታቸውን ለጦር ሜዳ እንዲቀይሩ ይወተውታል።
የዘመቻው ማስታወቂያ የብሪታንያ ወታደራዊ መረጃ እና የሩስያ መገናኛ ብዙኸን ሞስኮ እስከ 400 ሽህ የሚደርሱ ወታደሮችን "በበጎ ፈቃደኝነት" ለመመልመል ጥረት እያደረገች ነው ማለታቸውን ተከትሎ የመጣ ነው።
የሞስኮን ወታደራዊ ሚስጢሮች አሳልፎ የሰጠው የሩሲያ ኮማንደር
ሞስኮ ምልመላውን እያካሄደች ያለው በዩክሬን ያለውን ኃይሏን ለማጠናከር በማለም ነው ተብሏል።
የምልመላ ዘመቻ ማስታወቂያው እስካሁን በዋና ዋና የሩሲያ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ተለቋል።
ሩሲያ "ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ" በምትለው ጦርነት የሟቾችን ቁጥር አልገለጸችም ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።
ነገር ግን በቅርቡ ከአሜሪካ የመከላከያ የስለላ ኤጀንሲ ሾልኮ በወጣ መረጃ፤ በጦርነቱ እስከ 43 ሽህ የሚደርሱ ሩሲያውያን ተገድለዋል ይላል።
እስከ 17 ሽህ 500 የሚደርሱ የዩክሬን ወታደሮች እንደተገደሉ ይሄው ሾልኮ የወጣው መረጃን ዋቢ አድርጎ ሮይተርስ ዘግቧል።
በአዲሱ የሩሲያ ወታደራዊ ምልመላ ማስታወቂያ መሰረት አንድ ወታደር በወር ከ ሁለት ሽህ 495 ዶላር ጀምሮ ወርሃዊ ደመወዝ ይከፈላቸዋል፡፡