ሩሲያ፥ ማዕቀብ የተጣለበትን የነዳጅ ምርቷን ወደ ወዳጅ ሀገራት መላኬን ቀጥያለሁ አለች
ምዕራባውያን የዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ አንስቶ የሩሲያን አቅም ለማዳከም ሰፊ ማዕቀቦችን ጥለዋል
ሞስኮ ባለፈው ዓመት 42 ከመቶ በጀቷን ከነዳጅ ገቢ መሸፈኗ ተነግሯል
ሩሲያ በምዕራቡ ዓለም በድፍድፍ ነዳጅ ምርቷ ላይ የተጣለባትን ማዕቀብ ወደ "ወዳጅ" ሀገራት ማዘወሯን ተናገረች።
ሞስኮ በዩክሬን ጦርነት ምዕራባውያን የሩስያ ነዳጅ ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ እገዳን ጨምሮ ሰፊ ማዕቀቦችን ጥለዋል።
የሀገሪቱ የኢነርጂ ሚንስትር ኒኮላይ ሹልጊኖቭ "በእገዳው የተጎዱትን አጠቃላይ የወጪ ንግድ መጠን ሙሉ በሙሉ ማዞር እንደቻልን ዛሬ መናገር እችላለሁ። የሽያጭ ቅናሽ አልነበረም" ብለዋል።
ሹልጊኖቭ በፈረንጆቹ 2023 የሩሲያ የነዳጅ እና የጋዝ ምርት ይቀንሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል።
- ሩስያ እና ኢራንን ከማዕቀብ የታደገው የንግድ መስመር የትኛው ነው?
- ሳኡዲ አረቢያ በ2022 ለቻይና ከፍተኛውን የድፍድፍ ነዳጅ መጠን ያቀረበች ሀገር መሆኗ ተገለጸ
ለዚህም ምክንያቱ ሞስኮ በምዕራባውያን እገዳዎች እና በአውሮፓ ገዢዎች እጥረት ጫና ውስጥ መሆኗ ነው ብለዋል።
የሩስያ ግዙፉ የነዳጅ ዘይት አቅራቢ ጋዝፕሮም ዋና ስራ አስፈጻሚ አሌክሳንደር ዲዩኮቭ 2023 ከ2022 የበለጠ አስቸጋሪ እንደሚሆን እና የእገዳው ጫና እየጨመረ እንደሚሄድ ገልጸዋል።
የኢነርጂ ሚንስትሩ ሩሲያ የነዳጅ እና የዘይት ምርቷን ከአውሮፓ ገበያዋ ወደ እስያ፣ አፍሪካ፣ ላቲን አሜሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ አቅጣጫ ለመቀየር ስትሰራ ቆይታለች ብለዋል።
ህንድ በመጋቢት ወር የሩሲያን ድፍድፍ በመግዛት ቀዳሚ ሆናለች።
በፈረንጆች 2022 42 በመቶው የሩሲያ የፌደራል በጀት ከኃይል ገቢ እንደተሸፈነ ሮይተርስ ዘግቧል።