ሳኡዲ አረቢያ በ2022 ለቻይና ከፍተኛውን የድፍድፍ ነዳጅ መጠን ያቀረበች ሀገር መሆኗ ተገለጸ
ሩሲያ ለቻይና ነዳጅ በማቅረብ ዋናዋ የሳኡዲ አረቢያ ተቀናቃኝ ሆና እየመጣች ነው
ሳኡዲ አረቢያ በ2022 ብቻ 1 ነጥብ 75 ሚሊየን ድፍድፍ ነዳጅ ወደ ቻይና ልካለች
ከፍተኛ የነዳጅ ላኪዋ ሳኡዲ አረቢያ ለቻይና ከፍተኛውን የድፍድፍ ነዳጅ መጠን ያቀረበች ሀገር መሆኗ ተገለጸ፡፡
የቻይና የጉምሩክ አስተዳደር መረጃ እንደሚያሳየው ሳኡዲ አረቢያ ባሳለፍነው አመት በአጠቃላይ 87.49 ሚሊዮን ቶን (1.75 ሚሊየን በርሚል) ድፍድፍ ነዳጅ ወደ ቻይና መላኳን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
በተያያዘ በቻይናም ሆነ በእስያ ያላውን ገበያ ለማጠናከር እየታተረች የምትገኘው ሪያድ ለአህጉሪቱ ገዥዎች በ15 ወራት ውስጥ የድፍድፍ ነዳጅ የዋጋ ቅነሳ ልታደርግ እንደምትችል በቅርቡ ማስታወቋ አይዘነጋም፡፡
ሳኡዲ የዋጋ ቅነሳ የምታዳርገው የዓለም የነዳጅ ገበያ ላይ ባለው ከመጠን በላይ አቅርቦት ምክንያት ነው ተብሏል፡፡
በተለይም ነዳጇን በአውሮፓ ምድር እንዳትሸጥ እገዳ የተጣለባት ሩሲያ የነዳጅ ምርቷን ወደ እስያ ገበያ መላክ መጀመሯ ሳዑዲ አረቢያ በነዳጅ ዋጋ ላይ ቅነሳ እንድታደርግ አስገዳጅ ሁኔታ እንደፈጠረባት ይነገራል፡፡
ከሩሲያ -ዩክሬን ጦርነት ጋር በተያያዘ ከምዕራበውያን ጋር የነበራት የንግድ ልውውጥ ሙሉ በሙሉ ያቋረጠችው ሞስኮ ፊቷን ወደ ቻይና ማዞሯ የሚታወቅ ነው፡፡
ቢዘህም አሁን ላይ ድፍድፍ ነዳጅን ወደ ቻይና በማቅረብ ከሳኡዲ አረቢያ ቀጥሎ ሁለተኛዋ ሀገር መሆን ችላለች፡፡
ሀገሪቱ ከአንድ ዓመት በፊት በ2021 ወደ ቻይና ከላከችው 86.25 ሚሊዮን ቶን ድፍድፍ ነዳጅ በ2022 የ8 በመቶ እድገት ማሳየቱም ነው መረጃዎች የሚጠቁሙት፡፡
የዩክሬን ጦርነትን ተከትሎ በርካታ መዕቀቦችን ያስተናገደቸው ሞስኮ በዓለም አቀፍ የነዳጅ መለኪያዎች መሰረት በድፍድፍ ነዳጇ ላይ የዋጋ ቅናሽ በማድረግ በእስያ ቀደ ሚገኙ ቁልፍ የነዳጅ ደንበኞቿ እየላከች ነው፡፡
ይሁን እንጅ ሞስኮ የድፍድፍ ነዳጅ ሽያጩ በሩሲያ ድፍድፍ ነዳጅ ላይ የዋጋ ጣሪያን ለሚመለከቱ ሀገራት አይመለከትም ብላለች፡፡
በተጨማሪም ከሩሲያ -ዩክሬን ጦርነት ጋር በተያያዘ ከምዕራበውያን ጋር የነበራት የንግድ ልውውጥ ሙሉ በሙሉ ያቋረጠችው ሞስኮ፤ የተጣሉባት ማዕቀቦች የማይነሱ ከሆነ ወደ አውሮፓ ነዳጅ እንደማትልክ መግለጿ አይዘነጋም፡፡