ፖለቲካ
ሩሲያ፣ ዩክሬን በክሪሚያ ድልድይ ላይ ላደረሰችው ጥቃት አጸፋዊ ምላሽ እሰጣለሁ አለች
አሜሪካን ጨምሮ በምዕራባውያን በምትደገፈው ዩክሬን እና በሩሲያ መካከል ያለው ጦርነት እንደቀጠለ ነው
ሩሲያ በክሪሚያ ድልድይ ጥቃት በማድረስ "የሽብር ጥቃት"በፈጸመችው ዩክሬን ላይ አጸፋዊ ምላሽ እንደምትሰጥ አስታውቃለች
ሩሲያ በክሪሚያ ድልድይ ጥቃት በማድረስ "የሽብር ጥቃት"በፈጸመችው ዩክሬን ላይ አጸፋዊ ምላሽ እንደምትሰጥ አስታውቃለች
በክሪሚያ ድልድይ ላይ የደረሰውን ጥቃት ያወገዘው የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጥቃቱ የንጹሃንን ህይወት አደጋ ላይ መጣሉን እና አጸፋዊ ምላሽ እንደሚሰጥ ገልጿል።
"ለዚህ ጭካኔ የተሞላበት ድርገት ምንም ምክንያት ሊቀርብለት አይችልም፤ ምላሽ ይሰጣል" ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ማሪያ ዘካሮቫ ተናግረዋል።
ቀደም ሲል የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር የሩሲያ ጦር ሩሲያ በከርች ባህረሰላጤ በኩል በፈረንጆቹ 2014 ወደ ግዟቷ ካካተተቻት ክሪሚያ ጋር በሚያገናኘው የ19 ኪ.ሜ. ድልድይ ላይ የተቃጣ ጥቃት ማክኸፉን ገልጿል።
ሚኒስትሩ ክሪሚያ ኢላማ ያደረጉ በርካታ ድሮኖችን መትቶ መጣሉንም ማስታወቁ ይታወሳል
አሜሪካን ጨምሮ በምዕራባውያን በምትደገፈው ዩክሬን እና በሩሲያ መካከል ያለው ጦርነት እንደቀጠለ ነው