የአረብ ሀገራት በዩክሬን የጦርነት ጉዳይ “ኃላፊነት የተሞላበት አቋም ወስደዋል”- ሩሲያ
በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል የተቀሰቀሰው ግጭት አራት ወራት አልፎታል
ሩሲያ የአረብ ሀገራት ምእራባውያን ዩክሬንን በመጠቀም በሩሲያ ላይ እየፈጠሩት ያለውን የደህንነት ስጋት ተረድተዋል አለች
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቨሮቭ የአረብ ሀገራት በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል እየተካደ ባለው ጦርነት ላይ ኃላፊነት የተሞላበት አቋም ወስደዋል፤ በዚህም በራሳቸው ብሄራዊ ጥቅም ላይ ብቻ እንደሚቆሙ አረጋግጠዋል ብለዋል፡፡
ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከአርቲ ቴቪዥን ጋር ባደረጉት ቆይታ ለማንኛውም አካል የጆኦፖለቲካ ጥቅም ሲሉ የራሳቸውን ብሄራዊ ጥቅም አሳልፈው እንደማይሰጡም አይተናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ከአረብ ሀገራት ጋር በመከባበር ላይ የተመሰረተ ግንኙነት እንዳላቸው የጠቀሱት ላቭሮቭ ይህም የደህንነትን ለማስጠበቀቅ መሰረታዊ ነው ብለዋል፡፡
ሩሲያም ተመሳሳይ አካሄድ ትከተላለች ብለዋል ለቭሮቭ፡፡
ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የአረብ ሀገራት ምእራባውያን ዩክሬንን በመጠቀም በሩሲያ ላይ እየፈጠሩት ያለውን የደህንነት ስጋት መረዳታቸውን ገልጸዋል፡፡
ሩሲያ በዩክሬን ላይ “ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ” የጀመረችው፣ ዩክሬን የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት(ኔቶ) አባል ለመሆን እየተንቀሳቀሰች ነው፤ይህ ለደህንነቴ ያሰጋኛል በሚል ነበር፡፡
ከጦርነቱ መጀመር ቀደም ብሎ ኔቶ ወደ ቀድሞ የሶቬት ሀገራት የሚያደርገውን መስጋፋፋት እንዲያቆም ስትጠይቅ ነበር፡፡
ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ አሜሪካን ጨምሮ ምእራባውያ ሀገራት ሩሲያን ያዳክማል ያሉት ማእቀብ ሁሉ አዝንበዋል፡፡ ሩሲያም በበኩሏ ማእቀቡን ለመቋቋም የተለያዩ እርምጃዎችን ስትወስድ ቆይታለች፡፡
ሩሲያ ምእራባውያን ሀገራት ለሚገዙት ነዳጅ ክፍያው በሩብል እንዲያደርጉ መወሰኗ ምእራባውያን ሀገራትን ክፉኟ ያስቆጣ ጉዳይ ሆኗል፡፡