በሩሲያ ላይ የተጣሉትን ማእቀቦች የማንሳት ጉዳይ ከዩክሬን ጋር የሚደረገው ድርድር አንድ አካል ነው- ላቭሮቭ
"ድርድሩ ለአዳዲስ ጂኦፖለቲካዊ እውነታዎችን እውቅና መስጠት እና የሩስያ ቋንቋ ሁኔታን የሚሉ አጀንዳዎች ያካትታል"ም ብሏል
ፕሬዝዳንት ዜለንስኪ፤ “ማእቀብ ማንሳት የድርድሩ አካል” መሆን እንደሌለበት እየገለጹ ነው
በሩሲያ ላይ የተጣሉትን ማዕቀቦች ማንሳት ከዩክሬን ጋር የሚደረገው ድርድር አንድ አካል ሆነው እንደቀጠሉ ናቸው ሲሉ የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ተናገሩ፡፡
ላቭሮቭ፤ በሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ድረ-ገጽ ላይ ለታተመው የቻይናው የዜና ኤጀንሲ ዢንዋ በሰጡት አስተያየት “በአሁኑ ጊዜ የሩሲያ እና የዩክሬን ልዑካን በቪዲዮ ኮንፈረንስ በየእለቱ እየተወያየቱ ነው” ብሏል፡፡
"ድርድሩ ለአዳዲስ ጂኦፖለቲካዊ እውነታዎችን እውቅና መስጠት፣ ማዕቀቦችን ማንሳት እና የሩስያ ቋንቋ ሁኔታን የሚሉ አጀንዳዎች ያካትታል"ም ብሏል ሰረጌ ላቭሮቭ፡፡
ላቭሮቭ ይህን ይበሉ እንጂ፤ የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ዜለንስኪ፤ ምእራባውያን በሩሲያ ላይ የሚጥሉት ማእቀብ አጠናክረው እንዲቀጥሉና “ማእቀብ ማንሳት የድርድሩ አካል” መሆን እንደሌለበት እየገለጹ ነው፡፡
በተጨማሪወም አሁን የሩሲያ ኃይሎች እያካሄዱት ያለው መጠነ ሰፊ ወታደራዊ ዘመቻ፤ የተጀመረው ድርድር ውድቅ እንዳይሆን ያላቸውን ስጋትንም ገልጿል ዜለንስኪ፡፡
በሌላ በኩል ኪቭ አርብ ዕለት እንዳስጠነቀቀው፣ አሁን ሶስተኛ ወሩን ያስቆጠረውን የሩሲያን ወረራ ለማስቆም ንግግሮች የመውደቅ አደጋ ተጋርጦባቸዋል።
የዩክሬን እና ሩሲያ ባለስልጣነት ከመጋቢት 29 ወዲህ ፊት ለፊት ተገናኝተው እንዳልተወያዩ የሚታወቅ ነው፡፡ ምክንያቱም ደግሞ ሩሲያ ወታደራዊ ኃይሎች ከኪቭ አቅራቢያ ወደ ኋላ ባፈገፈጉበት ወቅት በንጹሃን ዩከሬናውያን ላይ ፈጽመውታል የተባለው ሰብዓዊነት ላይ ያነጣጠረ ወንጀልን ተከትሎ ነው፡፡
ላቭሮቭ "ድርድሩ አስቸጋሪ ቢሆንም እንዲቀጥል ደጋፊ ነን" ሲሉም አክሏል።
የሩሲያ-ዩክሬን ከተከሰተ ወዲህ፤ የዩክሬን ምዕራባውያን አጋሮች በሞስኮ ላይ ከፍተኛ ማዕቀብ ጥለዋል።
በዚህም ከሩሲያ ግዛት ግማሹን የወርቅ እና የውጭ ምንዛሪ ክምችት በመታገዱ ምክንያት፣የሩሲያን ኢኮኖሚ ኩፉኛ እንደተጎዳ ዓለም አቀፍ የምጣኔ ሃብት መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡