ቻይና፤ ከሩሲያ ጋር ያላትን ግንኙነት ለዓለም "አዲስ ሞዴል" የሚሆን ነው ስትል ገለጸች
አዲሱ የግንኙነት ሞዴል “ግጭቶችን የማያመጣና ሌሎችን ዒላማ የማያደርግ ነው”ም ብላለች ቻይና
ቻይና በዩክሬን ጉዳይ ሩሲያን አለማውገዟ ለአሜሪካና አጋሮቿ ምቾት እንዳልሰጣቸው ይታወቃል
ቻይና፤ ከሩሲያ ጋር ያላትን ግንኙነት ለዓለም "አዲስ ሞዴል" የሚሆን ነው ስትል ገልጸች፡፡
አሜሪካን ጨምሮ ሌሎች ሀገራት፤ ሩሲያ በዩክሬን ላይ የጀመረችውን ወታደራዊ ዘመቻ ቤጂንግ እንደትቃወም ይሹ የነበረ ቢሆንም፤ ቻይና ግን በተቃራኒው ለሩሲያ በንግግር ደራጃ የድጋፍ አቋማን ማንጸባረቋ ቀጥላበታለች፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዣኦ ሊጂያን ለብሉምበርግ ኒውስ እንደተናገሩት “የቻይና-ሩሲያ ግንኙነት ስኬት ካስገኛቸው አስፈላጊ ውጤቶች አንዱ ሁለቱ ወገኖች በቀዝቃዛው ጦርነት ላይ የነባረቸውና ጎልቶ የወጣው ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ አጋርነት ነው”ብሏል።
ሀገራቱ አዲስ “የዓለም አቀፍ ግንኙነት ሞዴል” ለማሳደግ እየታተሩ ነው ሲሉም አክሏል፡፡
ዣኦ ሀገራቱ ሚከተሉት የዓለም አቀፍ ግንኙነት ሞዴል ግጭቶችን የማያመጣ እንዲሁም ሌሎችን ዒላማ የማያደርግ ነው ብለዋል፡፡
አዲሱ ሞዴል የተወሰኑ ሀገራት ከሚከተሉት የ“ቀዝቃዛ ጦርነት አስተሳሰብ” የተለየ አካሄድ መሆኑንም አክሏል።
“አሜሪካ ከሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል-ኪዳን ድርጅት/ኔቶ/ ጋር የምታደርገውንና መስፋፋተን ያለመና አሁን ወደ ገባንባት ጦርነት የሚወስድ አይነት አይደለም” ሲሉም በምእራባውያን ላይ ያነጣጠረ ትችት አዘል ማብራሪያም ሰጥቷል ቃል አቀባዩ፡፡
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የቻይናው አቻቸውን ዢ ጂንፒንግ ቤጂንግ ሞስኮን በወረራ ምክንያት የምትደግፈውን ከሆነ ወጤቱ ጥሩ ላይሆን እንደሚችል ባለፈው ወር ማስጠንቀቃቸው አይዘነጋም፡፡
በወቅቱ ለጆ-ባይደን ምላሽ የሰጡት የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ በበኩላቸው “ቻይና ጦርነት አትፈልግም” ማለታቸው የሚታወስ ነው፡፡
የቻይና እና ሩሲያ አጋርነት ለአሜሪካ ምቾት የሰጣት አይመስልም፡፡ በተለይም በቅርቡ በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል የተፈጠረውን ጦርንት ተከትሎ ቻይና ፤ እንደ ምዕራቡ ዓለም ሀገራት ሩሲያን በግልጽ አለማውገዟ በአማሪካና አጋሮቿ በስጋት እንድትታይ እንዳደረጋት ይገለጻል፡፡
ከዚህም ባሻገር የሩሲያ አላት ተብሎ ከሚገመተው ወታደራዊ አቅምና ከቻይና ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ጋር ተዳምሮ፤ ዓለም አቀፉ ዲፕሎማሲ መስተጋበር ተለውጦ፤ የኃያልነት በትሩ አንዳቀበሉት የሚለው ስጋት ምእራባውያንን እንቅልፍ የነሳ ጉዳይ እንደሆነ ይነሳል፡፡