የሩሲያው ጋዝፕሮም የነዳጅ ሻጭ ኩባንያ ለሁለቱ ጎረቤት ሀገራት ፖላንድ እና ቡልጋሪያ ነዳጅ መሸጡን አስታውቋል
ሩሲያ ለፖላንድ እና ቡልጋሪያ ነዳጅ መሸጥ ማቆሟን ገለጸች፡፡
የሩሲያው ጋዝፕሮም የነዳጅ ሻጭ ኩባንያ ለሁለቱ ጎረቤት ሀገራት ፖላንድ እና ቡልጋሪያ ነዳጅ መሸጡን አስታውቋል፡፡
ኩባንያው ነዳጅ መሸጡን ያቆመው ሁለቱ ሀገራት የሩሲያ መንግስት ነዳጅ በሩብል እንዲሸጥ የወሰነውን ውሳኔ ባለማክበራቸው እንደሆነ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ኩባንያው አክሎም ሁለቱ ሀገራት ነዳጅ ለመግዛት የግድ ሩብል የሚያስፈልጋቸው ሲሆን ሩብል እስካልከፈሉ ድረስ እገዳው እንደሚቀጥልም ገልጿል፡፡
የክሬን የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ኔቶ ጦርን እቀላቀላለሁ ማለቷን ተከትሎ ሩሲያ ወደ ጦርነት ከገባች ሁለት ወራት ያለፈው ሲሆን አሜሪካንን ጨምሮ በርካታ የምዕራባዊያን ሀገራት በሩሲያ ላይ ማዕቀቦችን ጥለዋል፡፡
ሩሲያም ወዳጅ አይደሉም ባለቻቸው ሀገራት ላይ ነዳጅ በሩብል እንዲገዙ የሚያስገድድ አዲስ ውሳኔ ማስተላለፏ ይታወሳል፡፡
ውሳኔውን ተከትሎም የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን እንዳስታወቀው የአውሮፓ ነዳጅ ሻጭ ኩባያዎች ከሩሲያ ነዳጅን በሀገሪቱ መገበያያ ገንዘብ በሆነው ሩብል መግዛት እነምደሚችሉ አስታውቋል፡፡
እንደ ሮይተርስ ዘገባ ኩባንያዎቹ ነዳጅ ከሩሲያ በሩብል መግዛት የሚችሉት የአውሮፓ ህብረት በሩሲያ ላይ የጣለውን ማዕቀብ በማይጋፋ መንገድ እንዲሆንም ኮሚሽኑ አሳስቧል፡፡
ይሁንና እነዚህ የአውሮፓ ነዳጅ ሻጭ ኩባንያዎች ህብረቱ በሩሲያ ነዳጅ ላይ የጣለውን ማዕቀብ እንዴት ማክበር እንዳለባቸው የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን አላብራራም፡፡
ይህ በዚህ እንዳለም ሩሲያ የዩክሬን ቁልፍ የወደብ ከተማ የሆነችው ማሪዮፖል ከተማን ተቆጣጥሬያለሁ ያለችው ሩሲያ ደቡብ እና ምስራቅ ዩክሬን ለመቆጣጠር አዲስ ዘመቻ መጀመሯን ገልጻለች፡፡
ዩክሬን በበኩሏ ማሪዮፖል ከተማ እስካሁን በሩሲያ ጦር በቁጥጥር ስር አለመዋሏን ገልጻ በደቡባዊ ዩክሬን ከተሞች ላይ አዲስ ጥቃት እንደተከፈተባት አስታውቃለች፡፡
ሩሲያ በዩክሬን ላይ ጦርነት መክፈቷን ተከትሎ ምእራባውያን ሀገራት አሜሪካን ጨምሮ ሩሲያን ያዳክማል ያሉት ማእቀብ ሁሉ በመጣል ላይ ናቸው፡፡