የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ዩክሬን ዛፖሬዥያ የኑክሌር ጣቢያን ለመያዝ ያደረገችውን ሙከራ አከሸፍኩ አለ
ሩሲያ እና ዩክሬን ኑክሌር ጣቢያውን በማጥቃት እርስበእርስ እየተወነጃጀሉ ነው
ሩሲያ ድርጊቱ የታቀደውን የተመድ የኑክሌር ተቆጣጣሪዎችን ጉብኝት የሚያውክ ትንኮሳ ነው ብላለች
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር በዛሬው እለት የዩክሬን ኃይሎች የዛፖሬዥያ የኑክሌር ጣቢያን ለመያዝ ያደረጉትን ሙከራ ማክሸፉን አስታውቋል።
የዩክሬንን ጥቃት ለመከላከል አሰፈላጊው እርምጃ ተወሰዷል ያለው ሚኒስቴሩ 60 የሚሆኑ የዩክሬን ታጣቂዎች ሩሲያ እና ዩክሬን የተቆጣጠሩትን ቦታ የሚለየውን ድኒፕሮ ወንዝ አቋርጠው ነበር ብሏል።
ሚኒስቴሩ ይህ ድርጊት የታቀደውን የተመድ የኑክሌር ተቆጣጣሪዎችን ጉብኝት የሚያውክ ትንኮሳ ነው ብሏል።
የኒውክሌር ተቆጣጣሪ ቡድን በዩክሬን ወደ ሚገኘውና በሩሲያ ኃይሎች ቁጥጥር ስር ወዳለው ዛፖሪዝሂያ የኒውክሌር ጣቢያ አቅንቷል፡፡
ቡድኑ ወደ ኑክሌር ጣቢያው ያቀናው ሩሲያ ፍቃድ ከሰጠች በኃላ ነው።
ዛፖሪዝሂያ የኒውክሌር ጣቢያ በጦርነቱ ምክንያት በአከባቢው ላይ መጠነ ሰፊ የተኩስ ልውጦች እየተካሄዱ ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ፤ በኒውክሌር ጣቢያው ላይ ጥቃት ከደረሰ የጨረር አደጋ እንዳያስከትል በርካቶች ስጋታቸው ሲገልጹ ቆይተዋል፡፡
ሩሲያ እና ከዩክሬን ከአውሮፓ ትልቅ የሆነውን እና በዩክሬን የሚገኘውን የኑክሊየር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ላይ ጥቃት በማድረስ እርስ በእርሳቸው በመካሰስ ላይ ናቸው።
በደቡባዊ ዩክሬን የሚገኘው እና ሩሲያ በዩክሬን “ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ” እንደጀመረች በሩሲያ ጦር ቁጥጥር ስር የዋለው የዛፖሪዝሂያ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ጥቃት ደርሶበታል ተብሏ