ሩሲያ ያለባትን የውጭ ሀገራት እዳ በራሷ ገንዘብ “ሩብል” እንደምትከፍል አስታወቀች
የአሜሪካ ግምጃ ቤት ሩሲያ በአሜሪካ ባንኮች በኩል የምትፈጽመውን የውጭ ዕዳ ክፍያ ፍቃድ ሰርዟል
አሁን ላይ ሩብል ከሌሎች ሀገራት ገንዘብ ጋር ያለው ምንዛሬ የተረጋጋ መሆኑ ተነግሯል
ሩሲያ ያለባትን የውጭ ሀገራት እዳ በራሷ መገበያያ ገንዘብ “ሩብል” እንደምትከፍል አስታውቃለች።
የሩሲያ ምክር ቤት (ዱማ) ሊቀመንበር የሆኑት ቨያቸህስላቭ ቮሎዲን በቴሌግራም በሰጡት አስተያየት ነው፤ ሩሲያ ያለባትን የውጭ እዳ በሩብል ለመክፈል መዘጋጀቷን ያስታወቁት።
ሊቀ መንበሩ አክለውም ለሁሉም ፈንዶች የሚያስፈልጉ ክፍያቸዎችን በሩብል ለመክፈል ዝግጅት መደረጉንም አስታውቀዋል።
ሩሲያ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰችውም የአሜሪካ ግምጃ ቤት ባለፍነው ማሰኞ በሩሲያ በአሜሪካ ባንኮች በኩል የምትፈጽመውን የውጭ ዕዳ ክፍያ ፍቃድ መሰረዙን ተከትሎ ነው።
የሀገሪቱ ፋይናንስ ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫም፤ ሩሲያ እዳዋን ለመክፈል በቂ ገንዘብ አላት፤ ያሉባትን እዳዎች በሩብል ለመክፈልም ሙሉ ዝግጁ ነች ብለዋል።
አሁን ላይ ሩብል ከሌሎች ሀገራት ገንዘብ ጋር ያለው ምንዛሬ የተረጋጋ መሆኑ ተነግሯል።
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን፤ የሩሲያ ኢኮኖሚ ከምዕራቡ ዓለም የተጣለውን የማዕቀብ ውርጅብኝ መቋቋሙን ገልጸዋል።
በያዝነው ሳምንትም የሀገሪቱ ፋይናንስ ሚኒስቴር፤ ቀደም ሲል ኩባንያዎች ከሚያከናውት ሽያጭ 80 በመቶውን በውጭ ምንዛሬ እንዲያከናውኑ የተጣለው መመሪያ ማሻሻያ መደረጉን መግለጹ ይታወሳል።
የሩሲያ ኩባንያዎች ምርታቸውን ሲሸጡ 50 በመቶውን ብቻ በውጭ ምንዛሬ እንዲያደርጉ ተወሰነላቸው።
ሩሲያ ነዳጅን በውጭ ሀገራት መገበያያ ገንዘብ ሳይሆን በራሷ ሩብል እንደምትሸጥ መግለጿም የሚታወስ ሲሆን፤ ይህንን ተከትሎም በርካታ የአውሮፓ ሀገራት የሩብል ሂሳብ መከፍት መጀመራው እ ነዳጅን በሩብል ለመግዛት መስማማታቸውም ይታወሳል።