ሩሲያ ዩክሬን ጥቃቱን የፈጸመችው አሜሪካ ስራሽ በሆነ ሮኬት መሆኑን ገልጻለች
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በሩሲያ በሚደገፉ ተገንጣይዮች በተያዘው የዶንባስ ግዛት ውስጥ 40 የዩክሬን የጦር ምርኮኞች ዩክሬን በተኮሰችው ሚሳየል መገደላቸውን ገለጸ
ጥቃቱ የተፈጸመው አሜሪካ ሰራሽ በሆነው HIMARS ሮኬት መሆኑን የገለጸው ሚኒስቴሩ፣ ከሞቱት በተጨማሪ 75 መቁሰላቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ሮይተርስ የጦር ሜዳ ሪፖርቱን ማረጋገጥ እንደማይችል ገልጿል።
መከላከያ ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ በአንድ ጊዜ ብዙ መተኮስ በሚችለው አሜሪካ ስራሽ ሮኬት በደረሰው ጥቃት በእስር ላይ በነበሩ የጦር ምርኮኞች ላይ ጥቃት ማድረሱን አስታውቋል።
በአዞቭ ብርጌዶ የነበሩ እስረኞች ጭምር የሚገኙበት ቦታ ጥቃት ደርሶበታል ብሏሎ ሚኒስቴሩ።
ሚኒስቴሩ እንደገለጸው 40 የጦር ምርኮኞች ሲገደሉ ሌሎች 75 የሚሆኑ ደግሞ ቆስለዋል። በስምንት የእስር ቤቱ ሰራቸኞች ላይ ደግሞ ጉዳት መድረሱንም ሚኒስቴሩ ገልጿል።
ሩሲያ የኔቶ ጦር ወደ ቀድሞ የሶቬት ሀገራት መስፋፋት ለደህንነቷ እንደማያሰጋት በመግለጽ ነበር በዩክሬን ላይ "ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ" ያወጀችው።
ከዚህ በተጨማሪም ዩክሬንን ትጥቅ ማስፈታት እና የናዚን አስተሳሰብ ማጥፋት የዘመቻው አላማ መሆኑን ሩሲያ መግለጿ ይታወሳል።
በሩሲያ ርምጃ የተቆጡት ምእራባውያን ሩሲያን ያዳክማል ያሉትን ሁሉ ማእቀብ በሩሲያ ላይ ጥለዋል። የዶምባስ ግዛትን ነጻ የማውጣት የወሰነቸው ሩሲያ አሁንም በደቡብ እና ምሰራቃዊ ዩክሬን ጦርነት እያካሄደች ትገኛለች፡