ሩሲያ ከ100 በላይ አሜሪካ ሰራሽ "HIMARS" ሮኬቶችን “አወደምኩ” አለች
የዩክሬን ጦር ከአሜሪካ የተበረከተላትን የረጅም ርቀት ሮኬት ስርዓት መጠቀም መጀመሩን ገልጻ ነበር
ሩሲያም ምዕራባውያን ለዩክሬን የተለገሱትን የጦር መሳሪያዎች በማውደም ላይ መሆኗን ገልጻለች
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር በትናትናው እለት፣ የሩሲያ ጦር ባሳለፍነው ሐምሌ 16 በወሰደው እርምጃ ከ100 በላይ አሜሪካ ሰራሽ "HIMARS" ሮኬቶችን ማውደሙን አስታውቋል።
ሮኬቶቹ የወደሙት በዩክሬን ዲኒፕሮፔትሮስኮሽ ክልል መሆኑንም ሩሲያ አስታውቃለች።
ሩሲያ ባሳለፍነው ሰኞ አሜሪካ ለዩክሬን የሰጠቻቸውን ከባድ መሳሪያዎችን ኢለማ በማድረግ በፈጸመችው ጥቃት እንደሆነ አስታውቃለች።
በሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ላይ የኪቭ ከፍተኛ አጋር እና የጦር መሳሪያ አቅራቢ የሆነቸው አሜሪከ ባሳለፍነው ሳምንት ለዩክሬን ተጨማሪ 16 "HIMARS" ሮኬቶችን መለገሷን ገልጻለች።
ብሪታኒያም ተጨማሪ የረጅም ርቀት የጦር መሳሪዎችን ለዩክሬን መለገሷን አስታውቃለች።
ዩክሬን ከአሜሪካ የተበረከተላትን "HIMARS" የረጅም ርቀት ሮኬቶችን በውጊያ ላይ መጠቀም እንደጀመረች ገልጻ ነበር።
ሩሲያ ከዚህ ቀደምም ምእራባውያን ለዩከሬን የለገሱትን "HIMARS" የረጅም ርቀት ሮኬቶችን እንዳወደምች ገልጻ ነበር።
በተጨማሪም ሩሲያ በተደጋጋሚ ምእራባውያን ለዩክሬን የለገሱትን መሳሪያ የያዙ መጋዝኖችን እንዳወደምች መግለጿ ይታወሳል።
ምዕራባዊያን ሀገራት ለዩክሬን የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን በመለገስ ላይ ሲሆኑ፤ ሩሲያም የተለገሱትን የጦር መሳሪያዎች በማውደም ላይ መሆኗን ገልጻለች።
የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አሜሪካ እና ሌሎች ምዕራባዊያን ሀገራት ለዩክሬን የጦር መሳሪያ እንዳይለግሱ አሳስበው ልገሳቸውን ከቀጠሉ ግን እርምጃ መውሰዴን እንደሚቀጥሉማስጠንቀቃቸው ይታወሳል።
ዩክሬን የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ጦር ወይም ኔቶን እቀላቀላለሁ ማለቷን ተከትሎ ከሩሲያ ጋር ይፋዊ ጦርነት ከጀመረች ወራት ተቆጥረዋል።