ሩሲያ ምዕራባውያን ለዩክሬን አዲስ ታጣቂ ተሽከርካሪዎችን የሚሰጡ ከሆነ "ስቃዩን አጠናክራለሁ" አለ
ፈረንሣይና ጀርመን ለኪየቭ የሚያደርጉትን ወታደራዊ ድጋፍ በማጠናከር ቀላል የጦር ተሽከርካሪዎችን ወደ ዩክሬን እንደሚልኩ ባለፈው ሳምንት አስታውቀዋል
ሞስኮ ድጋፎቹ የሚያመጡት የዩክሬንን ህዝብ ስቃይ መጨመር እና ስቃያቸውን ማራዘም ብቻ ነው ብላለች
ሩሲያ ፈረንሳይ ሰራሽ የታጠቁ ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ ምዕራባውያን የጦር መሳሪያዎችን ወደ ኪየቭ መላካቸው የዩክሬንን ህዝብ ስቃይ እንደሚያባብሰው እና የግጭቱን አቅጣጫ እንደማይለውጥ ተናግሯል።
ፈረንሣይና ጀርመን ለኪየቭ የሚያደርጉትን ወታደራዊ ድጋፍ በማጠናከር ቀላል የጦር ተሽከርካሪዎችን ወደ ዩክሬን እንደሚልኩ ባለፈው ሳምንት አስታውቀዋል።
አሜሪካም ለዩክሬን የታጠቁ የጦር መኪኖችን እንደምትሰጥ አስታውቃለች።
የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት "ይህ አቅርቦት ምንም ነገር መለወጥ አይችልም" ብለዋል።
ፔስኮቭ "እነዚህ አቅርቦቶች የሚያመጡት የዩክሬንን ህዝብ ስቃይ መጨመር እና ስቃያቸውን ማራዘም ብቻ ነው። የልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ግቦችን እንዳናሳካ ሊከለክሉን አይችሉም" ብለዋል።
ሮይተርስ እንደዘገበው ዩክሬን የግጭቱን ሚዛን ለመጠበቅ ስትል የምዕራባውያን አጋሮችን ተጨማሪ ከባድ የጦር መሳሪያ እና የአየር መከላከያ ጠይቃለች።
ክሬምሊን ሰኞ ዕለት እንዳስታወቀው ምንም እንኳ ፈረንሳይ ወደ ኪየቭ ተጨማሪ የጦር መሳሪያ ለመላክ ብትወስንም፤ ሞስኮ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በምዕራቡ ዓለምና በሩሲያ መካከል ውይይት ለማስቀጠል ላደረጉት አስተዋፅኦ ታደንቃለች ብሏል።
ቃል አቀባዩ የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና ማክሮን ግንኙነታቸውን ይቀጥላሉ ብለዋል።