የዩክሬን ፕሬዝዳንት ዘሌንስኪ ሩሲያ ለገና በዓል ያቀረበችውን የእርቅ ትዕዛዝ “ማደናበሪያ” በሚል ውድቅ አደረጉ
የዩክሬን ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ከፈረንጆቹ 2019 ጀምሮ ራሷን ከሩሲያ ነጻ በማድረግ እውቅና አግኝታለች
ብዙ የዩክሬን አማኞች እንደ ምዕራቡ ዓለም ገናን ታህሳስ 25 ለማክበር የቀን መቁጠሪያቸውን መቀየራቸው ተሰምቷል
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ በኦርቶዶክስ ኃይማኖት ሞስኮ ለገና በዓል ያቀረበችውን እርቅ ውድቅ በማድረግ፤ ጦራቸው በምስራቅ ዶንባስ አካባቢ ያለውን ግስጋሴ ለማስቆም “ብልሃት” ነው ብለውታል።
ዘለንስኪ በሩሲያኛ በማተኮር በአጠቃላይ ለክሬምሊን እና ሩሲያውያንን ሲያነጋግሩ፤ ሞስኮ የኪየቭን የሰላም እቅድ ደጋግማ ችላ ብላለችል ሲሉ ወቅሰዋል። ጦርነቱ የሚያበቃው የሩሲያ ወታደሮች ዩክሬንን ለቀው ሲወጡ ወይም ስናስወጣቸው ነው ብለዋል።
"አሁን በዶንባስ ያሉ ልጆቻችንን ግስጋሴ ለማስቆም እና መሳሪያዎችን፣ ጥይቶችንና ወታደሮችን ወደ ሀገራችን ለማስገባት ለአጭር ጊዜ ቢሆንም ገናን እንደ ሽፋን ሊጠቀሙበት ይፈልጋሉ"
ሲሉ ዘሌንስኪ በተለመደው የምሽት መልዕክታቸው ተናግረዋል።
"ይህ [እርቁ] ምን ይሰጣቸዋል? ለኪሳራቸው ሌላ ጭማሪ ብቻ ነው" ሲሉም አክለዋል።
የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን በጎርጎሮሳዊያኑ የዘመን ቀመር ጥር ሰባት ላይ ገናን ታከብራለች።
የዩክሬን ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ከ2019 ጀምሮ በቤተክርስቲያኑ ተዋረድ ነጻ በመሆን እውቅና ማግኘቷን የጠቀሰው ሮይተርስ፤ ለሞስኮ ፓትርያርክ ተገዥ አይደለሁም በሚል በእግሯ ቆማለች።
ብዙ የዩክሬን አማኞች እንደ ምዕራቡ ዓለም ገናን ታህሳስ 25 ለማክበር የቀን መቁጠሪያቸውን ቀይረዋልም።
ዘሌንስኪ ጦርነቱን ማቆም ማለት "የሀገራችሁን ወረራ ማቆም ማለት ነው” ሲሉ ለሞስኮ ተናግረዋል።ዓለምን ለሁለት የከፈለው የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት ከተቀሰቀሰ አንድ ዓመት ሊደፍን ነው።