ዩክሬን "በበቂ ሁኔታ ደክማለች"- የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር
ሚኒስትሩ ሩሲያ በዩክሬን እየተደረገ ያለውን ዘመቻ ለመሸፈን በቂ ወታደሮች እና በጎፈቃደኞች እንዳሏት ገልጸዋል
ሾይጉ የሩሲያ ጦር የዩክሬንን የመዋጋት አቅም ትርጉም ባለው መልኩ ማዳከም ችሏል ብለዋል
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ሰርጌይ ሾይጉ ዩክሬን "በበቂ ሁኔታ ደክማለች" ሲሉ ተናግረዋል።
ሾይጉ የሩሲያ ጦር የዩክሬንን የመዋጋት አቅም ትርጉም ባለው መልኩ ማዳከም ችሏል ብለዋል።
ጠላት ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶበታል ሲሉ ሽይጉ በሞስኮ በተካሄደ የወታደራዊ አመራሮች ስብሰባ ላይ ተናግረዋል።
ዩክሬን በቅርቡ በባክሙት እና ሶለዳር ያደረሰችው ጥቃት መቀልበሱን የገለጹት ሚኒስትሩ በዛፖሮዥያ ግዛትም የሩሲያን የመከላከያ መስመር ለመስቀር ያደረገችው ጥረትም አልተሳካም ብለዋል።
የሾይጉ መግለጫ ስኬታማ ጥቃት በማድረስ ቦታዎች ማስለቀቋን ከገለጸችው ዩክሬን ጋር የሚጋጭ ነው።
ሚኒስትሩ ሩሲያ በዩክሬን እየተደረገ ያለውን ዘመቻ ለመሸፈን በቂ ወታደሮች እና በጎፈቃደኞች እንዳሏት ገልጸዋል።
ሾይጉ እንደገጹት አሁን 355ሺ ፈቃደኞች የሩሲየን ጦር ለቀላቀል ተመዝግበዋል፤ በመስከረም ወር ብቻ 50ሺ ሰዎች ለወታደራዊ አገልግሎት ኮንትራት ፈርመዋል።
ተጨማሪ ምልመላ አያስፈልግም ብለዋል ሾይጉ።
የሩሲያ እና ዩክሬንን ጦርነት በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመፍታት የደረጉ ሙከራዎች ለውጥ አላመጡም።
ሩሲያ እና በምዕራባውያን በምትደገፈው ዩክሬን መካከል የጀመረው ጦርነት አሁንም እንደቀጠለ ነው።