ሀገራቱ የሩሲያን ነዳጅ በርካሽ ከማግኘታቸው ባለፈ የእስያ ጋዝ ግብይት መተላለፊያም እንደሆኑ ተገልጿል
ሩሲያ የማዕከላዊ እስያ ሀገራትን ኢኮኖሚ ማሳደጓ ተገለጸ።
የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ 18ወራትን ያስቆጠረ ሲሆን እስካሁን እልባትም አልተገኘለትም።
ጦርነቱን ተከትሎ ምዕራባዊያን በሩሲያ መንግሥት እና ባለጸጋዎች ላይ ማዕቀብ መጣላቸውን ተከትሎ ለእስያ ሀገራት ግን ጥሩ እድል ማስገኘቱን ዩሮ ኒውስ ዘግቧል።
ጦርነቱ በተለይም ለማዕከላዊ እስያ ሀገራት ሲሳይ ሆኖላቸዋል የተባለ ሲሆን በርካታ ሩሲያዊያን ባለጸጋዎች ማዕቀብ ሽሽት ሀብታቸውን ይዘው ወደነዚህ ሀገራት ገብተዋል ተብሏል።
እንዲሁም የሩሲያ መንግሥት የጣለውን የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ በመሸሽ በርካታ ሩሲያዊያን ወደ ታጅኪስታን፣ ኡዝቤክስታን፣ ካዛኪስታን እና ኪርጊስታን መሸሻቸው ተገልጿል።
ሩሲያም በተለይም በአውሮፓ እና አሜሪካ ሀገራት ዜጎች ላይ በተራዋ ማዕቀብ መጣሏን ተከትሎ የማዕከላዊ እስያ ሀገራት ዜጎች ወደ ሞስኮ በቀላሉ እንዲገቡ እና የስራ እድል እንዲፈጠርላቸው በማድረጉ ሀገራቱ የውጭ ምንዛሬ ገቢያቸው እንዲሰፋ አድርጓልም ተብሏል።
ይህን ተከትሎም የማዕከላዊ እስያ ሀገራት በሩሲያ ምክንያት ኢሎኖሚያቸው እንዲነቃቃ እንዳደረገላቸው ተገልጿል።
ከዚህ በተጨማሪም እነዚህ ሀገራት ሩሲያ ነዳጇን ወደ እስያ ሀገራት የምትልከው ነዳጅ መጠኑ እንዲጨምር እና አቅርቦት አለመቆራረጡ ሀገራቱን መጥቀሙ ተገልጿል።
ሩሲያ በተጣለባት ማዕቀብ ምክንያት የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳያጋጥም በሚል የእስያ ሀገራት በርካታ ምርቶቻቸውን ወደ ሞስኮ እንዲልኩ መፍቀዷ ትልቅ የገበያ እድል አግኝተዋልም ተብሏል።