ሩሲያ በሳኡዲ አረቢያ ይካሄዳል የተባለውን ንግግር አላማ መረዳት እፈልጋለሁ አለች
ሩሲያ በሳኡዲ አረቢያ በዩክሬን ጉዳይ ይካሄዳል የተባለው ንግግር አላማ ምን እንደሆነ መረዳት እንደምትፈልግ ገለጸች
የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ዘለንስኪ በአንጻሩ ሩሲያ በወረራ የያዘችውን የዩክሬን ግዛት ሳትለቅ ንግግር የማይታሰብ ነው ሲሉ መናገራቸው ይታውሳል
ሩሲያ በሳኡዲ አረቢያ በዩክሬን ጉዳይ ይካሄዳል የተባለው ንግግር አላማ ምን እንደሆነ መረዳት እንደምትፈልግ ገለጸች።
ክሬሚሊን በዩክሬን ጦርነቱ ዙሪያ በሳኡዲ አረቢያ ይካሄዳል ስለተባለው ንግግር አላማ ማወቅ እንደሚፈልግ ተናግሯል።
የአሜሪካው ጋዜጣ ወልስትሪት ጆርናል ባለፈው ቅዳሜ እንደዘገው በሳኡዲ በዩክሬን ጉዳይ ይካሄዳል በተባለው ንግግር ላይ ምዕራባውያን ሀገራት፣ ዩክሬን እና ዋናዋና በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት ይጋበዛሉ።
ጋዛጣው እንደሚለው ከሆነ ሩሲያ በሌለችበት የሚካሄደው ንግግር ለዩክሬንን ፍላጎት የሚያደላ አለምአቀፍ ድጋፍ ለማግኘት እንደሚረዳ ምዕራባውያን እና ዩክሬን ተስፋ ጥለውበታል።
ስለወልስትሪት ጆርናል ሪፖርት ዘገባ የተጠየቁት የክሬሚሊን ቃል አቀባይ ዲሜትሪ ፔስኮቭ "በእርግጥ ሩሲያ ይህን ስብሰባ ትከታተለዋለች። ምን ግብ እንደተቀመጠ እና በምን ጉዳይ ውይይቱ እንደተካሄደ መረዳት አለብን። ሰላም ለማምጣት የሚደረግ ማንኛውም ሙከራ በአዎንታ መታየት ይገባዋል።" ብለዋል።
ነገርግን ፔስኮቭ እንደተናገሩት በአሁኑ ወቅት ከዩክሬን ጋር ለመነጋገር የሚያስችል መሰረት የለም በማለት የሩሲያን አቋም ግልጽ አድርገዋል።
ፔስኮቭ የኪቭ መንግስት ለሰለም ፍላጎት የለውም ሲሉም አክለዋል።
ፕሬዝደንት ፑቲን ባለፈው ቅዳሜ እንደተናገሩት ሩሲያ ከዩክሬን ጋር የሚደረግ የሰላም ንግግርን እንደማትቃወሞ ገልጸው ነበር።
ነገርግን ዩክሬን የጀመረችው መጠነ ሰፊ የማጥቃት ዘመቻ ሳይቆም የሰላም ንግግር ሊኖር እንደማይችል ተናግረዋል።
የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ዘለንስኪ በአንጻሩ ሩሲያ በወረራ የያዘችውን የዩክሬን ግዛት ሳትለቅ ንግግር የማይታሰብ ነው ሲሉ መናገራቸው ይታውሳል።