ሩሲያ ለስድስት የአፍሪካ ሀገራት 200ሺ ቶን እህል መላኳን ገለጸች
ሩሲያ ባለፈው ሀምሌ ወር ፕሬዝደንት ፑቲን ቃል በገቡት መሰረት ለስድስት ለስድስት ሀገራት በነጻ እህል መላኳን ገልጻለች
የሩሲያ የግብርና ሚኒስቴር እንደገለጸው ሞስኮ ባለፈው ሀምሌ ወር ፕሬዝደንት ፑቲን ቃል በገቡት መሰረት ለስድስት ሀገራት 200ሺ ቶን እህል አጓጉዛ ጨርሳለች
ሩሲያ ለስድስት የአፍሪካ ሀገራት 200ሺ ቶን እህል መላኳን ገለጸች።
የሩሲያ የግብርና ሚኒስቴር በትናንትናው እለት እንደገለጸው ሞስኮ ባለፈው ሀምሌ ወር ፕሬዝደንት ፑቲን ቃል በገቡት መሰረት ለስድስት ሀገራት 200ሺ ቶን እህል አጓጉዛ ጨርሳለች።
ሩሲያ ለዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ለሶማሊያ ለእያንዳንዳቸው 50ሺ ቶን እንዲሁም ለማሊ፣ ለቡርኪናፋሶ፣ ለዚምባብዌ እና ለኤርትራ ደግሞ ለእያንዳንዳቸው 25ሺ ቶን እህል ልካለች።
ሞስኮ፣ ዩክሬን እህሏን በቀይ ባህር ያለስጋት ለመላክ ከሚያስችላት "የጥቁር ባህር እህል ስምምነት" ከወጣች በኋላ ብዙም ሳትቆይ ነበር ፑቲን ባለፈው ሀምሌ ወር ከአፍሪካ መሪዎች ጋር ባደረጉት ስብሰባ ለስድስት ሀገራት በነጻ እህል እንደሚሰጡ ቃል የገቡት።
በቱርክ እና በተመድ አደራዳሪነት የተደረሰው 'የጥቁር ባህር የእህል ስምነት' አለምአቀፍ የእህል ዋጋ ዝቅ እንዲል አስችሎ ነበር። ነገርግን ፑቲን አስቸኳይ እርዳታ የሚፈልጉ ሀገራት እየደረሳቸው አይደለም የሚል መከራከሪያ አቅርበው ነበር።
የፑቲን የቅርብ ሰው የሆኑት ፖትሩሼቭ "ከሩሲያ-አፍሪካ ስብሰባ በኋላ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያለን ግንኙነት ጥሩ ደረጃ ላይ ነው" ብለዋል።
ፖትሩሼቭ ሩሲያ በ2023/2024 የምርት ዘመን 70 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን እህል ወደ ውጭ ለመላክ አቅዳለች። ሩሲያ ባለፈው የምርት ዘመን 66 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን እህል ወደ ውጭ ልካ 16.5 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቷን ፖትሩሼቭ ተናግረዋል።