ቱርክ የአየር ክልሏን መዝጋቷን ፕሬዚዳንት ፑቲን እንዲያውቁት ማድረጓን አስታውቃለች
ቱርክ ወደ ሶሪያ ለሚበሩ የሩሲያ አውሮፕላኖች የአየር ክልሏን እንደዘጋች የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜቭሉት ካቩሶግሉን አስታወቁ።
ሚኒስትሩ”ወደ ሶሪያ ለሚበሩ የሩሲያ ወታደራዊ እና ሲቪል አውሮፕላኖች የአየር ክልላችን ዘግተናል ” ማለቸውንም የቱርክ መገናኛ ብዙሃ ዘግበዋል።
የሩሲያ አውሮፕላኖች በክልላችን ላይ መብረር የሚችሉት እስከ ሚያዝያ ወር ብቻ እንደነበር ቀደም ሲል ስምምነት ነበረን ያሉት ካቩሶግሉ፤ ውሳኔውን ለሩሲያው አቻቸው ሰርጌይ ላቭሮቭ እንዳሳዉና ይህም የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን እንዲያውቁት መደረጉን ገልፀዋል።
ካቩሶግሉ ወደ ኡራጓይ በሚበረው አውሮፕላን ውስጥ ሆነው ለቱርክ ጋዜጠኞች በሰጡት ቃለ መጠይቅ “እገዳው ለሶስት ወራት ይቆያል” ብለዋል።
በቱርክ በኩል ለተላለፈው ውሳኔ በሩሲያ በኩል እስካሁን የተሰጠ ምላሽ እንደሌለም ነው የተገለጸው።
በፈረንጆቹ በ2015 በቱርክ-ሶሪያ ድንበር አቅራቢያ ላይ የሩሲያ የጦር አውሮፕላን በቱርክት ተመትታ ካወደቀች በኋላ የአንካራ -ሞስኮ ግንኙነት በተወሰነ መልኩም ቢሆን ላልቶ እንደነበር ይታወሳል።
ሆኖም ቱርክ፤ እንደ አስፈላጊ የንግድ እና ዲፕሎማሲያዊ አጋር አድርጋ ከምትመለከታት ሩሲያ ጋር ያላትን ግኙነት ለማጎልበት የተለያዩ ጥረቶች ስታደርግ ቆይታልች።
ስለ ሩሲያ-ዩክሬን ጦርነትና መፍትሄዎቹ የተጠየቁት የቱርኩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካቩሶግሉም "መሪዎቹ ስምምነት ከፈለጉ የማይቀር ነው" ብለዋል።