ሩሲያ ዊኪፒዲያ “ሀሰተኛ መረጃው”ን የማይሰርዝ ከሆነ እቀጣዋለሁ ስትል አስጠነቀቀች
ሩሲያ በዩክሬን “ወታራዊ ዘመቻ” መክፈቷን ተከትሎ በምእራባውያን እና በሩሲያ መካከል ውጥረት ነግሷል
ሩሲያ በዩክሬን ባካሄደችው “ወታራዊ ዘመቻ” እና በሩሲያ ጦር ድርጊት ዙሪያ ሀሰተኛ መረጃ ጭኗል በማለት ሩሲያ ዊኪፒዲያን ከሳለች
የሩሲያ የኮሙኒኬሽን ተቆጣጣሪ ሮስኮናድዞር ዊኪፒዲያ ስለዩክሬን ጉዳይ የጫነውን የተሳሳተ መረጃ እንዲሰርዝ እንደምትፈልግ አስታውቃለች፡፡
ተቆጣጣሪው እንደገለጸው ከሆኑ ሩሲያ በዩክሬን ባካሄደችው “ወታራዊ ዘመቻ” እና በሩሲያ ጦር ድርጊት ዙሪያ ሀሰተኛ መረጃ ጭኗል ሲል ክስ አቅርቧል፡፡
በሩሲያ ህግ መሰረት፤ በኢንተርኔት ላይ ያለው ጹህፍ ባለቤት በሩሲያው ተቆጣጣሪ እንዲያጠፋው ተጠይቆ የማያጠፋው ከሆነ እስከ 48 ዶላር ወይንም 4 ሚሊዮን ሩብልስ ያስቀጣል፡፡
ሩሲያ በዩክሬን ባደረገችው “ወታራዊ ዘመቻ” በርካታ ቦታወችን መቆጣጠር ችላለች፡፡
ምእራባውያን ፌስቡክን ጨምሮ ሌሎች ማህበራዊ ሚዲያ ተቋማት እንዳይሰሩ እግድ መጣላቸው ይታወሳል፡፡
ሩሲያ ወደ ግጭት የገባቸውም የኔቶ ጦር ዩክሬንን ጨምሮ ወደ ቀድሞ ሶቬት አባል ሀገራት እየተስፋፋ ነው ይህም ለደህንነቴ ያሰጋኛል በሚል ነበር፡፡ ሩሲያ እና ዩክሬን ወደ ግጭት ውስጥ ከገቡ በኋላ ምእራባውያን ሩሲያን ያዳክማል ያሉትን ሁሉንም አይነት ማእቀብ ጥለዋል፤እየጣሉም ነው፡፡
የሩሲያ መንግስት ቃል አቀባይ ዲሜትሪ ፓስኮቭ ከአሜሪካው ፒቢኤስ ጋር በደረጉት ቆይታ ሩሲያ ህልውናዋን አደጋ ውስጥ የሚከት ስጋት ካጋጠማት ብቻ የኑክለር ጦር መሳሪያ ልትጠቀም እንደምትችል ተናግረዋል፡፡
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ስለ ፑቲን ስልጣን መቆየት የሰጡት አስተያየት የሚረብሽ እና ግለሰብ ላይ ያነጣጠረ ስድብ ነው ያሉት ቃል አቀባዩ ኔቶ የመፋጠጫ ማሽን ነው ብለዋል፡፡
“በዩክሬን ውስጥ በምናደርገው ዘመቻ የኑክለር ጦር መሳሪያ የምንጠቀምበት ምክንያት የለም፣…እኛ ባለን ግልጽ ፖሊሲ ላይ እንደተቀመጠው የኑክለር ጦር መሳሪያ የምንጠቀም እንደሀገር መቀጠላችን አደጋ ከተጋረጠት ብቻ ነው፣ ስጋቱን ለማጥፋት ኑክለር እንጠቀማን” ብለዋል፡፡
ሩሲያ እና ዩክሬን ችግሩን ለመፍታት በቱርክ አመቻችነት እየተደራደሩ ይገኛል፡፡