የሱዳን ወታደራዊ መንግስት ለሩሲያ ጥያቄ አወንታዊ ምላሽ መስጠቱ ተገልጿል
ሩሲያ በቀይ ባህር የነዳጅ ማደያ ለመገንባት ጥያቄ ማቅረቧ ተገለጸ፡፡
በእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ያለችው ጎረቤት ሀገር ሱዳን ሩሲያ በቀይ ባህር የነዳጅ ማደያ እንትገነባ ጥያቄ እንደቀረበላት አስታውቃለች፡፡
በሱዳን ጦር ውስጥ አመራር የሆኑት ጀነራል ሰር አል አታ እንዳሉት ሱዳን የጦር መሳሪያ ድጋፍ ለማግኘት በሚል ከሩሲያ የቀረበላትን ጥያቄ እንደምትቀበል ተናግረዋል፡፡
ሁለቱ ሀገራት ይህን ስምምነት በቀርቡ ሊፈራረሙ እንደሚችሉ አል አረቢያ ጀነራል ያሰር አል አታን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል፡፡
ሩሲያ እስካሁን በሱዳን ጦር አመራር ይፋ ስለተደረገው የቀይ ባህር ነዳጅ ማደያ ግንባታ ዙሪያ በይፋ ያለችው ነገር የለም፡፡
ሩሲያ በቀድሞው የሱዳን ፕሬዝዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር አስተዳድር ጊዜ በፖርት ሱዳን ወታደራዊ ማዘዣ ለመገንባት ስምምነት ላይ ደርሰው ነበር፡፡
ፕሬዝዳንቱ በመፈንቅለ ስልጣን ከተወገዱ በኋላ ይህ ስምምነት ሳይተገበር እስካሁን የቆየ ሲሆን የሱዳን ወታደራዊ መንግስት ስምምነቱን እየገመገመ መሆኑን በተደጋጋሚ አስታውቋል፡፡
የትግራይ ታጣቂዎች በሱዳን ጦርነት መሳተፍ አለመሳተፋቸው እየተጣራ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታወቀ
በሱዳን በጀነራል አልቡርሃን የሚመራው የሀገሪቱ ጦር እና በጀነራል መሀመድ ሀምዳን ዳጋሎ ወይም ሄመቲ በሚመራው የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይሎች መካከል ጦርነት ከተቀሰቀሰ አንድ ዓመት አልፎታል፡፡
በዚህ ጦርነት ከ15 ሺህ በላይ ንጹሃን እንደተገደሉ የመንግስታቱ ድርጅት ሪፖርት ያስረዳል፡፡
በቀድሞው የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ የሚመራ የሲቪል ፖለቲከኞች ጥምረት ለሱዳን ጦርነት መቆም የሚረዳ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር እና ድርድር እንዲኖር እየሰራ ይገኛል፡፡