ሩሲያ በጦር ግንባሮች ስልክ የሚይዙ ወታደሮቿን የሚቀጣ ህግ አዘጋጀች
ዩክሬን እና ሩሲያ ስማርትሰ ልኮችን የሚጠቀሙ ወታደሮችን መረጃ በመውሰድ ጥቃት እየነዘሩ ናቸው
ሩሲያ ያዘጋጀችው አዲሱ ህግ ዘመናዊ ስልክ ይዘው የተገኙ ወታደሮችን እስከ 15 ቀናት እስር እንዲፈረድባቸው የሚያደርግ ነው
ሩሲያ በጦር ግንባሮች ስልክ የሚይዙ ወታደሮቿን የሚቀጣ ህግ አዘጋጀች፡፡
ሶስተኛ ዓመቱ ላይ የሚገኘው የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት አሁንም እንደቀጠለ ሲሆን በየጊዜው አዳዲስ ክስተቶች እየተመዘገቡበት ይገኛሉ፡፡
ሁለቱ ሀገራት አንዳቸው በሌላኛው ላይ የበላይነት ለመውሰድ ቴክኖሎጂዎችን አብዝተው እየተጠቀሙ ሲሆን በውጊያ ግንባሮች ያሉ ወታደሮችን አድራሻ መውሰድ አንዱ ነው፡፡
ዩክሬን ከአንድ ዓመት በፊት አዲ ዓመትን በጋራ እያከበሩ የነበሩ ከ100 በላይ የሩሲያ ወታደሮችን መግደሏ ይታወሳል፡፡
ሩሲያ አብዛኞቹን የጦር መርከቦቿን ያካተተ ልምምድ ጀመረች
ይህ የዩክሬን ጥቃት እንዲፈጸም ደግሞ ዘመናዊ ስልኮችን ሲጠቀሙ የነበሩ የሩሲያ ወተደሮችን አድራሻ በማግኘቷ ነበር፡፡
ሩሲያም ቁልፍ የዩክሬን ወታደረሮች ውጊያ ግንባሮች ያሉ ተዋጊዎችን አድራሻ በመጥለፍ በርካታ ጥቃቶችን እንዳደረሰች ተገልጿል፡፡
ይህን ተከትሎ የሩሲያ ህግ አውጪ ምክር ቤት ወታደሮች ዘመናዊ ስልኮችን ይዘው ወደ ውጊያ ግንባሮች እንዳይገቡ የሚከለክል ህግ አዘጋጅቷል፡፡
ይህን ረቂቅ ህግ ተላልፈው የተገኙ ወታደሮችም እስከ 15 ቀናት የሚዘልቅ እስር እንዲተላለፍባቸው ይፈቅዳል ሲል ታስ ዘግቧል፡፡