ፖለቲካ
ሩሲያና ዩክሬን የኒውክሌር ጣቢያ ላይ ጥቃትን በማሴር እርስ በእርሳቸው ተካሰሱ
ሁለቱ ወገኖች ጣቢያውን በመደብደብ ከፍተኛ የኒውክሌር አደጋ ይደርሳል በማለት ስጋት ላይ ናቸው
ሩሲያ ትልቁን የአውሮፓ የኒውክሌር ጣቢያ ጦርነቱ በተጀመረ ማግስት ተቆጣጥራለች
ሩሲያ እና ዩክሬን በሞስኮ ቁጥጥር ስር በሚገኘው የዛፖሪዝሂያ የኒውክሌር ኃይል ጣቢያ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር በማሴር እርስ በእርሳቸው ተወንጃጅለዋል።
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ ለፈረንሳዩ አቻቸው ኢማኑኤል ማክሮን በደቡብ ምስራቅ ዩክሬን በሚገኘው ጣቢያ ውስጥ የሩሲያን "አደገኛ ቅስቀሳዎች" እንደነገሯቸው አሳውቀዋል።
የሩስያ ወታደሮች ትልቁን የአውሮፓጰየኒውክሌር ጣቢያ የያዙት የካቲት 2022 ክሬምሊን "ልዩ ተልዕኮ" በሚል በጀመረችው ዘመቻ ማግስት ነበር።
ከዚህም ጊዜ ጀምሮ ሁለቱ ወገኖች ጣቢያውን በመደብደብ እና ከፍተኛ የኒውክሌር አደጋ ይደርሳል በማለት ክስ ይሰናዘራሉ።
የሩሲያ የኒውክሌር ጣቢያዎችን የሚያስተዳድረው የሮዝነርጎአቶም ኃላፊ አማካሪ ሬናት ካርቻአ፤ ዩክሬን ጣቢያውን ለመምታት አቅዳለች ብለዋል።
"ሀምሌ 5 ቀን ጨለማን ተገን በማድረግ የዩክሬን ጦር የረጅም ርቀት መሳሪያዎችን እና ድሮኖችን በመጠቀም በዛፖሪዝሂያ ጣቢያ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ይሞክሯል" ሲሉ ከሰዋል።
ሆኖም ግን ላቀረቡትት ክስ ምንም አይነት ማስረጃ አላቀረቡም።