የሩሲያ ጦር በምስራቅ ዩክሬን “ስኬታማ ወታደራዊ ዘመቻ” እያካሄደ መሆኑን ገለጸ
ሩሲያ፤ እየተባበሰ ለመጣው ጦርነት አሜሪካን እና አጋሮቿን ተጠያቂ አድርጋለች
በደም አፋሳሹ የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት 200 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ተገድለዋል ወይም ቆስለዋል ተብሎ ይገመታል
የሩሲያ ጦር በምስራቅ ዩክሬን የባክሙት እና ቩህሌዳር ከተሞች አቅራቢያ ስኬታማ ወታደራዊ ዘመቻ በማካሄድ እየገሰገሰ መሆኑን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ሰርጌ ሾይጉ ተናግረዋል።
"ወታደራዊ ዘመቻዎቹ በአሁኑ ጊዜ በቩህሌዳር እና በአርቴሞቭስክ አከባቢዎች በተሳካ ሁኔታ በመካሄድ ላይ ናቸው" ሲሉም ነው።
ሾይጉ በጥርሳዑዲ አረቢያ በሩሲያ ላይ የተጣለው ማዕቀብ የኃይል እጥረት ያስከትላል ስትል አስጠነቀቀች
ወር በሩሲያ ቁጥጥር ስር የወደቀችውና የጨው ማዕድን መገኛ የሆነውችን ሶላዳር ከተማን ጨምሮ ሩሲያ በቅርቡ “ነጻ ያወጣቻቸው” ሰባት አከባቢዎችን እንደ አብነት በማንሳት።
የመከላካያ ሚኒስትሩ፤ አሁን ላይ ለኪቭ በመሰጠት ላይ ያሉና ቃል የተገባ የጦር መሳሪያ አቅርቦት "ግጭቱን በተቻለ መጠን ለማራዘም የሚደረግ ሙከራ ነው” ሲሉም አሜሪካን እና የምዕራቡ ዓለም አጋሮቿን ከሰዋል፡፡
"እንዲህ ያሉት እርምጃዎች የኔቶ ሀሮችን ወደ ግጭት እንደገቡ የሚያደርጉና ባልተጠበቀ ሁኔታ ነገሮች የሚያባብሱ ናቸው" ሲሉም አክለዋል።
እንደ ሾይጉ ገለጻ፣ ዩክሬን ባለፈው ወር ከ6 ሺህ500 በላይ ወታደሮቿን ከማጣቷ በተጨማሪ 26 አውሮፕላኖችን፣ ሰባት ሄሊኮፕተሮችን እና 341 ታንኮችን አጥታለች።
የሩሲያ ጦር ረጅሙ እና ደም አፋሳሹ ጦርነት እየተካሄደበት ባለውና በዶኔትስክ ምስራቃዊ ክልል የሚገኘውን ባክሙትን ለመቆጣጠር ለወራት ሲሞክሩ ቆይተዋል።
የሩስያ ታዋቂው የዋግነር ቅጥረኛ ቡድን መሪ ዬቭጄኒ ፕሪጎዝሂን በሰሜናዊ በባክሙት ከባድ ጦርነት እየተካሄደ መሆኑን በቅርቡ መናገራቸውም አይዘነጋም፡፡
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ቅዳሜ እለት በሰጡት መግለጫ ለባክሙት “የምንችለውን ያህል” እንዋጋለን ሲሉ መደመጣቸውም የሚታወስ ነው፡፡
ኒው ዮርክ ታይምስ የምዕራቡ ዓለም መረጃን ጠቅሶ እንደዘገበው ከሆነ በደም አፋሳሹ የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት 200 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ተገድለዋል ወይም ቆስለዋል ተብሎ ይገመታል፡፡