ሳዑዲ አረቢያ በሩሲያ ላይ የተጣለው ማዕቀብ የኃይል እጥረት ያስከትላል ስትል አስጠነቀቀች
የአውሮፓ ህብረት የሩሲያን የኃይል አቅርቦት የሚቀንስ ተከታታይ ማዕቀቦችን ጥሏል
ሳዑዲ አረቢያ ለማብሰያና ለማሞቂያ የሚያገለግል ፈሳሽ ጋዝ ለዩክሬን እልካለሁ ብላለች
ሳዑዲ አረቢያ በሩሲያ ላይ የተጣለው ማዕቀብ የኃይል እጥረት ያስከትላል ስትል አስጠነቀቀች።
የሳዑዲ አረቢያ የኃይል ሚንስትር ልዑል አብዱላዚዝ ቢን ሳልማን ማዕቀብ እና በኃይል ዘርፍ አነስተኛ ኢንቨስትመንት የኃይል አቅርቦት እጥረትን ሊያስከትል ይችላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
የአውሮፓ ህብረት የሩሲያን የኃይል አቅርቦት የቀነሰ ተከታታይ ማዕቀቦችን ጥሏል። ሌሎች የምዕራባውያን ሀገራትም ሞስኮ ጦርነቱን ተከትሎ የገንዘብ አቅሟን ለመገደብ በሚል ተመሳሳይ እርምጃ ወስደዋል።
ምዕራባዊያን በሩሲያ ላይ እየወሰዱት ስላለው ማዕቀብ እንዴት እንደሚጎዳ ለተጠየቁት ጥያቄ ቢን ሳልማን ሲመልሱ “ ማዕቀቦች፣ እገዳዎች፣ የኢንቨስትመንት እጦት ወደ አንድ ነገር ብቻ ይጠቃለላሉ። ይህም በፍላጎት ጊዜ ሁሉም አይነት የኃይል አቅርቦቶች እጥረት እንዲገጥም ያደርጋል" ብለዋል።
ልዑሉ በንግግራቸው ውስጥ ሩሲያን በዋናነት አልጠቀሰም ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።
ሳዑዲ አረቢያ በብዛት ለማብሰያና ለማሞቂያ የሚያገለግለውን ፈሳሽ ጋዝ ለዩክሬን ለመላክ እየሰራች ነው ብለዋል።
ልዑል አብዱላዚዝ በፈረንጆቹ 2022 ከኃይል ገበያ ተለዋዋጭነት ምን ትምህርት እንደተገኘ ተጠይቀው በጣም አስፈላጊው የተቀረው ዓለም የነዳጅ ላኪዎች ህብረት “ኦፔክን ማመን” ነው ብለዋል።
"እኛ ኃላፊነት የሚሰማን የሀገራት ቡድን ነን። እናም እራሳችንን በፖለቲካ ጉዳዮች ውስጥ አናስገባም" ብለዋል ልዑሉ።
የነዳጅ ላኪ ሀገሮችን (ኦፔክ) እና ሩሲያን ጨምሮ ሌሎችን ያካተተው ኦፔክ ፕላስ ጥምረት ባለፈው ዓመት የምርት እቅዱን በቀን ሁለት ሚሊዮን በርሜል እንዲቀንስ ተስማምቷል። ይህም ከዓለም ፍላጎት ሁለት በመቶ የሚሆነው ነው።