የአሜሪካና እንግሊዝ የደህንነት መረጃዎች ተዓማኒ አለመሆናቸውን ሩሲያ ገለጸች
የሁለቱ ሀገራት የደህንነት መረጃዎች በኢራቅ እና በሌሎች አገራት ውድመትን አስከትለዋል ተብሏል
የሁለቱ ሀገራት የደህንነት መረጃዎች በኢራቅ እና በሌሎች አገራት ውድመትን አስከትለዋል ተብሏል
የአሜሪካ እና እንግሊዝ የደህንነት መረጃዎች ተዓማኒ አለመሆናቸውን ሩሲያ ገለጸች።
ዩክሬን የሰሜን አትላንቲክ ቃልኪዳን ጦር ወይም ኔቶን እቀላቀላለሁ ማለቷን ተከትሎ ሩሲያ ጉዳዩ የሉዓላዊነት ጉዳይ ነው በሚል ድርጊቱን እንደማትቀበለው አስታውቃለች።
በዚህ ምክንያትም በአሜሪካ የሚመራው ኔቶ ሩሲያ ዩክሬንን ልትወር ትችላለች በሚል ጦሩን ወደ ዩክሬን ድንበር አስጠግቷል።
ሩሲያም ከ150 ሺህ በላይ ጦር ወደ ዩክሬን ድንበሮች በተለያዩ አቅጣጫዎች ማስጠጋቷን ተከትሎ በምስራቅ አውሮፓ ውጥረት ነግሷል።
የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ከሰሞኑ በዩክሬን ጉዳይ የተሰበሰበ ሲሆን ሩሲያ ዩክሬንን እንደምትወር እርግጠኛ ሆና ብታስረዳም ጉዳዩ በሩሲያ ውድቅ ተድረጓል።
በጸጥታው ምክር ቤት የሩሲያ ምክትል ዋና መልዕክተኛ አምባሳደር ድሚትሪ ፖሌያንስኪ እንዳሉት የአሜሪካ እና የእንግሊዝ የደህንነት ተቋማት የሚያቀርቧቸው መረጃዎች ሀሰተኛ ናቸው ብለዋል።
የሁለቱ ሀገራት የደህንነት ተቋማት በዩክሬን ጉዳይ የሚያቀርቧቸው መረጃዎች የተሳሳቱ ናቸው ያሉት ቋሚ መልዕክተኛው ከዚህ በፊት በአሜሪካ መራሹ የኢራቅ ወረራ ምክንያት የደረሰውን ውድመት በዋቢነት አንስተዋል።
እነዚሁ ተቋማት አሁንም እንደለመዱት ሀሰተኛ መረጃዎችን በማውጣት ላይ መሆናቸውን እና ዩክሬንን የሚጎዱ መረጃዎችን ለዓለም በመልቀቅ ላይ መሆናቸውን በምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ መናገራቸውን ሮይተርስ ዘገቧል።
የሑለቱ አገራት የደህንነት መረጃዎችን አናምናቸውም፣የሩሲያ ወታደሮች በግዛታቸው የት እና እንዴት ወታደራዊ ልምምዶችን እንደሚያደርጉ መረጃ ለማግኘት አይችሉም ሲሉም አምባሳደር ድሚትሪ ተናግረዋል።