ፖለቲካ
“የኤምባሲ ሰራተኞችን ወይም የቤተሰቦቻቸውን አባላት ከሀገር የማስወጣት እቅድ የለም “- የሩሲያ ኤምባሲ
የሩሲያ ኤምባሲ ቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖት እንደሁል ጊዜ የተለመደውን ስራ እያከናወነ ነው ብሏል
ኤምባሲውም የተለመደና መደበኛ ስራውን እያከናወነ መሆኑንም ገልጿል
በአዲስ አበባ ከተማ ያለው ሁኔታ የተረጋጋ መሆኑን የሩሲያ ኤምባሲ ዛሬ ምሽት ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁ በኢትዮጵያ ዋና ከተማ የዕለት ተዕለት የኑሮ ዘይቤ እና እንቅስቃሴ ላይ ምንም አይነት ለውጥ አላመጣም ሲል ኤምባሲው ገልጿል።
- ሩሲያ በኢትዮጵያ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ በድጋሚ ጠየቀች
- "ድምፃችን ለነፃነታችንና ለሉዓላዊነታችን" በሚል በተካሔደው ሰልፍ ላይ ሩሲያ እና ቻይና ተመሰገኑ
ይሁን እንጂ አሁንም ቢሆን የሩሲያ ዜጎች ለአስቸኳይ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ወደ ሀገሪቱ ከመጓዝ እንዲቆጠቡ መክሯል።
ኤምባሲው እንደሁል ጊዜው የተለመደ ስራውን እያከናወነ መሆኑን የገለፀ ሲሆን ሰራተኞች ወይም የቤተሰቦቻቸውን አባላት ከሀገር የማስወጣት እቅድ እንደሌለ አሳውቋል።
የሩሲያ ኤምባሲ ቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖት እንደሁል ጊዜ የተለመደውን ስራ እያከናወነ መሆኑን የገለፀ ሲሆን የኢትዮጵያ ሲቪል አቬዬሽን ባለስልጣን በቅርቡ እንደገለፀው በሀገሪቱ የሚደረጉ በረራዎች ደህንነታቸው የተጠበቁ ናቸው ማለቱን አስታውሷል።
የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛራኮቫ ከዚኅ ቀደም በሸፁጽ መግለጫ፤ ሩሲያ የኢትዮጵያን ግዛት አንድነት መከበር ለድርድር የማይቀርብ እና ግጭቱን መፈቻ መንገድ ሊሆን እንደማይችል ታምናለች ማለታቸው ይታወሳል።