ዩክሬን ኔቶን የምትቀላቀል ከሆነ 3ኛው የዓለም ጦርነት ይነሳል ሲሉ የሩሲያ ባለስልጣን አስጠነቀቁ
ዩክሬን ኔቶን የምትቀላቀል ከሆነ 3ኛው የዓለም ጦርነት ይነሳል ሲሉ የሩሲያ ባለስልጣን አስጠነቀቁ
ፕሬዝዳንት ፑቲን የኔቶ ወደ ቀድሞ የሶቬት የሚያደረገውን መስፋፋት ተገቢ ከለመሆኑን በተደጋጋሚ አስጠንቅቀዋል።
የሩሲያው ባለስልጣን በዩክሬን ያለው ግጭት ወደ 3ኛው የአለም ጦርነት ያድጋል ብለው ማስጠንቃቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ዩክሬን በከምሪካ በሚመራው የኔቶ ወታደራዊ ጥምረት ውስጥ የምትገባ ከሆነ በዩክሬን ያለው ግጭት ወደ ሶስተኛው የዓለም ጦርነት እንደሚያድግ የሩሲያ የፀጥታው ምክር ቤት ባለሥልጣን ተናገሩ።
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ፑቲን በፈረንጆቹ መስከረም 18 በመቶ የሚሆነውን የዩክሬን ግዛት መቀላቀል በይፋ ካወጁ ከጥቂት ሰአታት በኋላ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ የናቶ አባል ለመሆን ፈጣን ጥሪ አቅርበው ነበር።
የዩክሬን ሙሉ የኔቶ አባልነት በጣም ሩቅ ነው ምክንያቱም ሁሉም የህብረቱ 30 አባላት ፈቃዳቸውን መስጠት አለባቸው።
ኪየቭ እንዲህ ዓይነቱ እርምጃ ወደ 3ኛው የዓለም ጦርነት እንደሚያሸጋግር ጠንቅቃ ታውቃለች ሲሉ የሩሲያ የፀጥታው ምክር ቤት ምክትል ፀሐፊ አሌክሳንደር ቬኔዲክቶቭን ለታስ የዜና ወኪል ተናግሯል።
የፑቲን አጋር የፀጥታው ምክር ቤት ፀሐፊ ኒኮላይ ፓትሩሼቭ ምዕራባውያን የዩክሬይን የኔቶ አባልነት የሚያስከትለውን መዘዝ ስለሚረዱ የዩክሬን ማመልከቻ ፕሮፓጋንዳ እንደሆነ ይሰማኛል ብሏል።
"እንዲህ ዓይነቱ እርምጃ ራስን የማጥፋት ባህሪ በኔቶ አባላት ራሳቸው የተረዱት ነው" ብለዋል።
ፕሬዝዳንት ፑቲን የኔቶ የምስራቅ መስፋፋት በተለይም ወደ ቀድሞ የሶቬት የሚያደረገውን መስፋፋት ተገቢ ከለመሆኑን በተደጋጋሚ አስጠንቅቀዋል።