ፑቲን የሩሲያ ሉአላዊነት ከተደፈረ ኑክሌር እንጠቀማለን ማለታቸው ለማስመሰል አለመሆኑን ለምዕራባውያን መናገራቸው ይታወሳል
ሩሲያ፤ አሜሪካ ወደ ጦር መሳሪያ ማምረት ውድድር እንዳትገባ አስጠነቀቀች።
አሜሪካ የሚቀጥለውን የጦር መሳሪያ ማምረት ውድድር አሸንፋለሁ ብላ የምትጠብቅ ከሆነ ተሳስታለች ሲሉ አንድ ከፍተኛ የሩሲያ ዲፕሎማት መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ዲፕሎማቱ ሩሲያ እና አሜሪካም ወደ ወታደራዊ ግጭት ሊያመሩ ይችላሉ ብለዋል።
የሩሲያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ርያብኮቭ እንደገለጹት ወቅታዊ ሁኔታው ከዋሽንግተን ጋር የጦር መሳሪያ ውድድር ለማድረግ አይመችም።
ርያብኮቮ "አሜሪካ የሚቀጥለውን የጦር መሳሪያ ምርት ውድድር አሸንለሁ ብላ የምታስብ ከሆነ ወይም ፕሬዝደንት ሮናልድ ሪገን ያደረጉትን የምትሞክር ከሆነ...አሜሪካ ተሳስታለች"ብለዋል።
ርያብኮቭ አክለውም "ለትንኮሳ አንበረከክም። ደህንነታችንን እናረጋግጣለን" ሲሉ ተናግረዋል።
የሩሲያው ፕሬዝደንት ፑቲን የሩሲያ ሉአላዊነት ከተደፈረ ኑክሌር እንጠቀማለን ማለታቸው ለማስመሰል አለመሆኑን ለምዕራባውያን መናገራቸው ይታወሳል።
ርያብኮቭ ሞስኮ ከኔቶ ጋር ግጭት ውስጥ መግባት ፍላጎት የላትም፤ ነገርግን የጥምረቱ ሁኔታ ይወስነዋል ብለዋል።
ሩሲያ በዩክሬን ላይ ልዩ ያለችውን ዘመቻ ከጀመረች በኋላ በሞስኮ እና በኔቶ መካከል ያለው የሀይለቃል ልውውጥ ጨምሯል።