ሩሲያ ከአሜሪካ ጋር የነበራትን የኒውክሌር ስምምነት ብታቋርጥም ለህጉ እገዛለሁ አለች
ስምምነቱ የእያንዳንዱን ሀገር የኒውክሌር ጦር በአንድ ሽህ 550 የሚገድብ ነው
ሞስኮ የኒውክሌር ስምሪቶችን ለዋሽንግተን አሳውቃለሁ ብላለች
ሩሲያ ከአሜሪካ ጋር የነበራትን የኑክሌር ውል ብታቋርጥም ለህጉ እንደምትገዛ ገለጸች።
ሩሲያ በኒውክሌር ሚሳይሎች ላይ የተደረሰውን ገደብ ማክበር እንደምትቀጥል እና ለውጥ ሲኖር ለአሜሪካ እንደምታሳውቅ ተናግራለች።
ሁለቱም የሩሲያ ምክር ቤቶች ሞስኮ የኒውክሌር ስምምነት ላይ የምታደርገውን ተሳትፎ እንድታግድ ድምጽ ተሰጥተዋል።
ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ማክሰኞ እለት ያስታወቁትን ውሳኔ በዩክሬን ላይ "ስልታዊ ሽንፈት" ለማድረስ ሲሉ ምዕራባውያንን ወቅሰውታል።
ነገር ግን ከፍተኛ የመከላከያ ሚንስቴር ባለስልጣን የሆኑት ሜጀር ጄኔራል ዬቭጄኒ ኢሊን ለታችኛው ምክር ቤት ሩሲያ በኒውክሌር ስርዓቶች ላይ ስምምነት የተደረሰባቸውን ገደቦችን ማክበር እንደምትቀጥል ገልጸዋል።
ይህም ሚሳይሎችን እና ስልታዊ የቦምብ አውሮፕላኖች ማለት ነው።
ሮይተርስ አርአይኤ የዜና ወኪልን ጠቅሶ እንደዘገበው ሞስኮ ስልታዊ መረጋጋትን ለመጠበቅ የኒውክሌር ማሰማራትን አስመልክቶ ለዋሽንግተን ማሳወቂያዎችን መስጠቷን ትቀጥላለች።
ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ሪያብኮቭም ይህኑ አረጋግጠዋል ነው የተባለው።
"አዲሱን የስታርት ስምምነት ለማቋረጥ መወሰኑ ወደ ኒውክሌር ጦርነት ይመራናል ብዬ አላምንም" ብለዋል።
ፕሬዝዳንት ፑቲን የሩሲያ "የግዛት አንድነት" አደጋ ላይ ከወደቀ የኒውክሌር መሳሪያ ለመጠቀም ፈቃደኛ ነኝ ሲሉ ተናግረዋል።
እ.አ.አ. በ 2010 የተፈረመው አዲስ ስታርት ስምምነት የእያንዳንዱን ሀገር የኒውክሌር ጦር በአንድ ሽህ 550 የሚገድብ ነው።
ይህን ስምምነትንም ሩሲያ ማክበሯን እንደምትቀጥል አስታውቃለች።