ቡርኪና ፋሶ በታሪኳ መጀመሪያውን የኦሎምፒክ ሜዳሊያ አገኘች
አትሌት ሁጎስ ፋብሪስ ዛንጎ በርዝመት ዝላይ ውድድር ላ3ኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ ለሀገሩ የነሃስ ሜዳሊያ አስገኝቷል
ቡርኪና ፋሶ ከ1972 የሙኒክ ኦሎምፒክ ጀምሮ 10 የኦሎምፒክ መድረኮች ላይ ተሳትፋለች
ቡርኪናፋ በታሪኳ የመጀመሪያውን የኦሎምፒክ ሜዳሊያ እየተካሄደ ባለው የ2020 የቶኪዮ ኦሎምፒክ ላይ አስመዘገበች።
የቡርኪና ፋሶው አትሌት ሁጎስ ፋብሪስ ዛንጎ በቶኪዮ ኦሎምፒክ የርዝመት ዝላይ ውድድር ላይ 3ኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ ለሀገሩ የነሃስ ሜዳሊያን አስገኝቷል።
ይህንን ተከትሎም አትሌቱ በኦሎምፒክ መድረክ ላይ ለቡርኪና ፋሶ የመጀመሪያውን ሜዳሊያ በማስገኘት አዲስ ታሪክ ጽፏል።
አትሌት ሁገስ ፋብሪስ ዛንጎ ያገኘው ሜዳሊያ በቶኪዮ ኦሎምፒክ ላይም ቡሪክና ፋሶን የሜዳሊያ ሰንርዥ ውስጥ የገባች 100ኛ ሀገር አድርጓታል።
ከዚህ ቀደም በዶሃ በተካሄደው የዓለም አትሌቲክ ውድድር ላይ ለሀገሩ የነሃስ ሜዳሊያ ያስገኘው የ28 ዓመቱ አትሌት ሁገስ ፋብሪስ ዛንጎ፤ በቶኪዮ ኦሎምፒክ ላይም 17.47 ሜትር በመዝለል ነው ለሀገሩ አዲስ ታሪክ ማስመዝገብ የቻለው።
በውድድሩ ፖርቹጋላዊው አትሌት ፔድሮ ፒካርዶ 17.98 ሜትር በመዝለል የወርቅ ሜዳሊያ ሲያገኝ፤ ቻይናዊዉ አትሌት ዙ ይማንግ 17.57 ሜትር በመዝለል የብር ሜዳሊያውን መውሰድ ችሏል።
ለሀገሩ የነሃስ ሜዳሊያን ያስገኘው የቡርኪና ፋሶው አትሌት ሁገስ ፋብሪስ ዛንጎ፤ በውድድሩ የወርቅ ሜዳሊያ የማግኘት እቅድ እንደነበረው ተናግሮ ነበር።
ቡሪክና ፋሶ በኦሎምፒክ መድረኮች ላይ መሳተፍ የጀመረችው እንደ አውሮፓውያኑ በ1972 በሙኒክ በተካሄደው ኦሎምፒክ ላይ እንደነበረ መረጃዎች ያመለክታሉ።
ሀገሪቱ በሶስት የኦሎምፒክ መድረኮች ላይ ማለትም በ1976 የሞንትሪያል ኦሎምፒክ፣ በ1980 የሞስኮ ኦሎምፒክ እንዲሁም በ1984 የሎስአንጀልስ ኦሎፒኮች ላይ አልተፋተፈችም።
በ1988 በደቡብ ኮሪያ አስተናጋጅነት በተካሄደው የሴኡል ኦሎምፒክ ላይ ወደ ውድድር የተመሰለችው ቡርኪና ፋሶ፤ እስከ 2020 የቶኪዮ ኦሎምፒክ ድረስ ተሳትፋለች።
የ9 የኦሎምፒክ መድረኮች ያለ ሜዳሊያ ጉዞም በ10ኛው የኦሎምፒክ ተሳትፎዋ የተገታ ሲሆን፤ ሀገሪቱ በታሪኳ የመጀመሪያውን የኦሎምፒክ ሜዳሊም በቶኪዮ ኦሎምፒክ ላይ የነሃስ ሜዳሊያ በማግኘት አንድ ብላ ጀምራለች።