የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር በዩክሬን የሚገኙ ወታደሮቻቸውን ጎብኙ
ሾይጉ በጦርነቱ ውስጥ ባሳዩት የአመራር ድክመት በርካታ ትችቶች ሲያስተናግዱ ይስተዋላል
ሚኒስትሩ ሾይጉ ከሩሲያ ወታደራዊ አዛዦች ጋር በመሆን በተለያዩ የጦር ግንባሮች ያለውን ሁኔታ ገምግመዋል
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ሰርጌይ ሾይጉ በዩክሬን የሚገኙትን የሩሲያ ወታደሮች መጎብኘታቸው ተገለጸ፡፡
የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር እንደገለጸው ሰርጌይ ሾይጉ ከሩሲያ ወታደራዊ አዛዦች በተለያዩ የጦር ግንባሮች ተገኝተው ሁኔታዎችን ገምግመዋል፡፡
ሚኒስትሩም ሆነ ወታደራዊ አዛዦቹ መሰል ጉብኝት ሲያደረጉ ሞስኮ በዩክሬን ምድር "ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ" ማካሄድ ከጀመረች ወዲህ የመጀመሪያው ነው ተብሎለታል፡፡
"የሩሲያ ፌዴሬሽን የመከላከያ ሚኒስትርና ሰርጌይ ሾይጉ በደቡብ ዶኔትስክ አቅጣጫ ያለውን የምስራቅ ወታደራዊ ዲስትሪክት የሚገኘውን ኮማንድ ፖስት ገብኝተዋል" ብሏል ሚኒስቴር በቴልግራም ገጹ ባሰራጨው በቪዲዮ የታገዘ መረጃ፡፡
ቪዲዮው ሚኒስትሩ ሾይጉ ለሩሲያ ወታደሮች ሜዳሊያ ሲሰጡና ከዲስትሪክቱ አዛዥ ኮሎኔል ሩስታም ሙራዶቭ ጋር በመሆን የፈራረሰች ከተማን ሲጎበኙ የሚያሳይ ነው፡፡
ከ2012 ጀምሮ የመከላከያ ሚኒስትር ሆነው በማገልገል ላይ ያሉት ሾይጉ በጦርነቱ ውስጥ ባሳዩት የአመራር ድክመት በርካታ ትችቶች ሲያስተናግዱ ይስተዋላል፡፡
ሾይጉን ከተቹት መካከል በጦርነቱ ጥሩ ሚና እየተጫወተ ያለውን የዋግንር ቅጥረኛ ቡድን ዋና አዛዥ ዬቭጄኒ ፕሪጎዚን ነቸው፡፡
ዬቭጄኒ ፕሪጎዚን በተለይም ለቡድኑ ሚሊሻዎች መሳሪያ በማቅረብ በኩል ለነበረው ክፍትት ሾይጉ "ክህደት" ተፈጽሞብናል ሲሉ ሾይጉን ከሰዋል፡፡