ባክሙትን መቆጣጠር የኢንዱስትሪ ክልል የሆነችው ዶንባስን በቁጥጥር ስር ለማዋል ትልቅ ወታደራዊ ፋይዳ እንዳለው ይነገራል
ወራት ከፈረጀው ደም አፈሳሽ ጦርንት በኋላ የሩሲያ ኃይሎች የምስራቅ ዩክሬኗን ባክሙት ከተማን ለመቆጣጠር መቃረባቸው እየተገለጸ ነው፡፡
የሩሲያ ኃይሎች አሁን ላይ ከተማዋን ለመቆጣጠር የሚያስችሏቸው ዋና ዋና መንገዶች ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት እየፈጸሙ እንደሆነም የሩሲያው የዋግነር ቡድን ጦር መሪ ተናግረዋል፡፡
ሮይተርስ ከባክሙት ወደ ምዕራብ በሚወስዱ መንገዶች ላይ ‘የዩክሬንወታደሮች ወደ ከተማዋ እንዳይገቡ የሚያደርጉ’ የሩሲያ ከፍተኛ ድብደባ መመልከቱን ገልጿል፡፡
በአቅራቢያው በምትገኘው ክሮሞቭ ከተማ የሚገኘው ድልድይም ጭምር በሩሲያ ታንኮች እንዲፈርስ ተደርጓል፡፡
የሩሲያው የዜና ወኪል አርአይኤ የዋግነር ተዋጊዎች በተበላሹ የኢንዱስትሪ ተቋማት ሲሄዱ የሚያሳይ ቪዲዮ አሰራጭቷል፡፡
የዩክሬን ወታደሮች አሁን ላይ ተስፋ ቆርጠው በባክሙት አቅራቢያ ባሉ ሰፈሮች መሰረተ ልማቶችን ማውደም መጀመራቸውም አንድ የሩሲያ ወታደርን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡
የዩክሬን ኃይሎች ባክሙትን ለመቆጣጠር መጠነሰ ሰፊ ጥቃት በመሰንዘር ላይ ቢሆኑም፤ የዩክሬን ጦር ከተማዋን ለመከላከል እየተዋደቀ ነው ተብሏል፡
የዩክሬን ወታደሮች የተበላሹ መንገዶችን እየጠገኑና አዳዲስ ምሽጎች እየቆፈሩም ጭምር ከተማዋን ከሩሲያ ኃይሎች ለመታደግ እየተዋጉ መሆናቸውም ተዘግቧል፡፡
የዩክሬን የምድር ጦር አዛዥ ኦሌክሳንደር ሲርስኪ በአካባቢው ከሚገኙት አዛዦች ጋር የሩሲያ ጥቃትን መቀልበስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ለመምከር ባክሙት ናቸው ተብሏል፡፡
በባክሙት የሚገኙት የዩክሬን ጦር አዛዥ ዴኒስ ያሮስላቭስኪ ለኤስፕሬሶ ቴሌቪዥን እንደተናገሩት፤ በባክሙት እሆነ ያለው ነገር "በሁለቱም በኩል የእርድ ቤት" ይመስላል ሲሉ ገልጸውታል፡፡
ከተማዋን ለማዳን አንዳንድ አሃዶች አስተማማኝ ወደ ሆኑ ወታደራዊ ይዞታዎች ላይ ሆነው እንዲዋጉ መታዘዛቸውም ተናግረዋል የጦር አዛዡ፡፡
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ባክሙትን ለመከላከል የሚደረገው ውጊያ ከባድ እንደሚሆነ ከቀናት በፊት መናገራቸው ይታወሳል፡፡
"ሩሲያ በአጠቃላይ ሰዎችን ህይወት ግምት ውስጥ አታስገባም እና የማያቋርጥ ማዕበል ትልካለች፤ የትግሉ ጥንካሬ እየጨመረ ነው"ም ነበር ያሉት ፕሬዝዳንቱ፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የዩክሬን ጦርነት እንዳሰቡት ያልሆነላቸው የክሬምሊን ባለስልጣናት ከጦርነቱ በፊት የ70,000 ያህሉ ዩክሬናውያን መኖሪያ የነበረችው ባክሙት የሚቆጣጠሩ ከሆነ፤ ከግማሽ አመት ደም አፋሳሽ ጦርነት በኋላ በክርምት ወቅት የሚቀዳጁት ትልቅ ድል ይሆናል፡፡
ባክሙት መቆጣጠር ማለት ከሞስኮ ዋና አላማዎች አንዱ የሆነውን የኢንዱስትሪ ክልል የሆነቸውን ዶንባስ በቁጥጥር ስር ለማዋል እንደ መሰላል ድንጋይ ሆኖ እንደሚጋለግልም ነው የወታደራዊ ሳይንስ ሊሂቃን የሚገልጹት፡፡