ሩሲያ እና ቱርክ በሶሪያ ጉዳይ የተለያዩ ወገኖችን ይደግፋሉ
የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ነገ ወደ ቱርክ መዲና አንካራ እንደሚያቀኑ የቱርክ ባለስልጣናት ገለጹ፡፡
ሚኒስትር ላቭሮቭ ወደ ዩክሬን እንደሚያቀኑ የተገለጸው በዩክሬን እና ሶሪያ ጉዳይ ላይ ለመመካር እንደሆነም ተገልጿል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በቱርክ ቆይታቸው ዩክሬን በጥቁር ባሕር በኩል ጥራጥሬ ወደ ውጭ በምትልክበት ሁኔታ ላይ እንደሚወያዩ ተገልጿል፡፡
ቱርክ የተባበሩት መንግስት ድርጅት ዩክሬን ጥራጥሬ እንድትልክ በጀመረው ጥረት ላይ እየተሳተፈች ነው፡፡ የሩሲያው መገናኛ ብዙሃን አርቲ በበኩሉ የሰርጌ ላቭሮቭ የቱርክ ጉብኝት ከዩክሬን ጋር ተጀምሮ የነበረው ንግግር እንዲመለስ ሊያደርግ እንደሚችል ዘግቧል፡፡
ቱርክ በጦርነት ውስጥ የሚገኙትን ዩክሬን እና ሩሲያን የምትቀርብ ሀገር በመሆኗ ንግግር እንዲጀምሩ ጥረት ስታደርግ ቆይታለች፡፡ ቱርክ ምንም እንኳን ሩሲያ ዩክሬንን እንደወረረች ብትገልጽም በሩሲያ ላይ የሚሉትን ማዕቀቦች አልደገፈችም፡፡
ሩሲያ እና ዩክሬን በዩክሬን ጉዳይ ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይት እንደሚኖራቸው በስፋት እየተዘገበ ቢሆንም የሶሪያን ጉዳይ አንስተው እንደሚነጋገሩም ተጠብቋል፡፡ ቱርክ በሰሜን ሶሪያ ያላትን ቆይታ እንድትቀጥል ከሩሲያ ፍቃድ ትፈልጋለች ተብሏል፡፡ ሩሲያ እና ቱርክ በሶሪያ ጦርነት ላይ ድጋፍ የሚሰጡት በተቃራኒ ጎራ ለተሰለፉት ሃይሎች ነው፡፡
ሩሲያ በምትደግፈው ሶሪያ የአየር ጥቃት በ 2020 ፣ 30 የቱርክ ወታደሮች መገደላቸው ይታወሳል፡፡ ቱርክ በሶሪያ የሚገኙት የኩርድ ታጣቂዎቸ የጸጥታ ስጋት መሆናቸውን በተደጋጋሚ ገልጻለች፡፡