የሩሲያ ኃይሎች ወደ ስትራቴጂካዊቷ የምስራቅ ዩክሬን ፖክሮቭስክ ከተማ ተቃረቡ
ከደቡብ ማጥቃት ያደረጉት የሩሲያ ኃይሎች ከከተማ በ1.5 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ደርሰዋል ተብሏል

የአሜሪካዋን አሪዞና ግዛት ያህል የተቆጣጠረችው ሩሲያ ልዩ ያለችውን ዘመቻ ከጀመረችበት ከ2022 ወዲህ በፍጥነት እየገሰገሱ ሆናቸው ተዘግቧል
የሩሲያ ኃይሎች ወደ ስትራቴጂካዊቷ የምስራቅ ዩክሬን ፖክሮቭስክ ከተማ ተቃረቡ።
ከደቡብ በኩል እየገፉ ያሉት የሩሲያ ኃይሎች ወሳኝ ከተባለች የፖክሮቭስክ ከተማ 1.5 ኪሎሜትር ርቀት ላይ መሆናቸውን የሩሲያ የጦር ጸኃፈዎችን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል።
የአሜሪካዋን አሪዞና ግዛት ያህል የተቆጣጠረችው ሩሲያ ልዩ ያለችውን ዘመቻ ከጀመረችበት ከ2022 ወዲህ በፍጥነት እየገሰገሱ ነው ተብሏል።
ዩክሬን የተወለደው ታዋቂው የሩሲያ ጦር ደጋፊ ጸኃፊ ዩሪ ፖዶሊያካ እንገለጸው ከደቡብ ማጥቃት ያደረጉት የሩሲያ ኃይሎች ከከተማ በ1.5 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ደርሰዋል።
የሩሲያ አሻጥረኞች፣ ቅኝት የሚያደርጉ እና ልዩ ኃይሎች ግንባሩን ጥሰው ከተማ ገብተዋል ብሏል ፖዶሊያካ።
ሮይተርስ ይህን ማረጋገጥ እንዳልቻለ ገልጿል።
በቅርቡ የዩክሬን ጦር የሩሲያ ኃይሎች በከተማዋ ዙሪያ ያሉ በርካታ ምሽጎችን ማውደማቸውን እና በርካታ የዩክሬን ምሽጎችን መያዛቸውን ገልጾ ነበር።
ፖክሮቭስክ በሩሲያ እጅ የምትገባ ከሆነ ዩክሬን በወራት ውስጥ ካጋጠሟት ኪሳራዎች ሁሉ ከባዱ ይሆናል ተብሏል።
የሩሲያ ሚዲያዎች "የዶኔስክ መግቢያ" የሚሏትን ከተማ መቆጣጠር ሩሲያ በምስራቅ በኩለ የዩክሬንን የአቅርቦት ሰንሰለት እንድትበጣጥስ እና ቻሲቭ ያር የተባለችውን ከተማ ለመያዝ የምታደርገውን ዘመቻ እንድታጠናክር ያስችላታል።
ሩሲያ የዩክሬን ወታደሮች ለመንገድ ያላቸውን ተደራሽነት በመገደብ፣ የዩክሬን ኃይሎች በየትኛው የከተማዋ አቅጣጫ ያሉ ቦታዎች ለመከላከል አደጋች እንዲሆንባቸው እና ሩሲያ ኃይሏን አጠናክራ ወደ ግንባር እንድትገፋ ሊረዳት ይችላል።
ከተማ በአንድ ወቅት እጅግ ግዙፍ ለነበረው የብረት ኢንዱትሪዋ የሚሆነው የከሰል ማዕድን ማውጫ ቦታ መገኛ ነች።