የአሜሪካ ወርሃዊ በጀት እጥረት 367 ቢሊዮን ዶላር ደረሰ
በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የደረሱ አደጋዎች ለመንግስት ወጪ መጨመር ትልቁ ምክንያት ሆነዋል
የአሜሪካ ብሔራዊ እዳ ከ36 ትሪሊየን ዶላር ተሻግሯል
የአሜሪካ ወርሃዊ በጀት እጥረት 367 ቢሊዮን ዶላር ደረሰ፡፡
የዓለማችን ልዕለ ሀያል ሀገር የሆነችው አሜሪካ ወርሃዊ በጀቷ የ367 ቢሊዮን ዶላር እጥረት አጋጥሞታል፡፡
እንደ ሮይተርስ ዘገባ ከሆነ ሀገሪቱ በተጠናቀቀው ሕዳር ወር ላይ የገጠማት የበጀት እጠረት ከፍተኛ ነው የተባለ ሲሆን ከአንድ ዓመት በፊት ከነበረው ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነጻጸር የ17 በመቶ ብልጫ አሳይቷል፡፡
ለመንግስት በጀት መጨመር ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩም በካሊፎርኒያ ያጋጠመው የእሳት አደጋ እና የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋዎች ዋነኞቹ ናቸው ተብሏል፡፡
እንዲሁም ለጤና እና ጡረተኞች የሚከፈሉ ክፍያዎች መጨመር ለመንግስት በጀት መጨመር ተጨማሪ ምክንያቶች ናቸው፡፡
የበጀት እጥረቱ በኮሮና ቫይረስ ወቅት በኋላ በታሪክ ከፍተኛ ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን የ2025 በጀት ዓመትም የበጀት ጉድለት ሊያጋጥመው እንደሚችልም ተሰግቷል፡፡
የፌዴራል መንግስት የ2017 አጠቃላይ በጀት 1.5 ትሪሊየን ብር ደረሰ
በአጠቃላይ የአሜሪካ መንግስት ብሄራዊ እዳ ከ36 ትሪሊየን ዶላር የተሸገረ ሲሆን ይህም በታሪክ ከፍተኛው ነው ተብሏል፡፡
ከቀናት በፊት ይፋ በተደረገው መረጃ ደግሞ የአሜሪካ መንግስት እዳ አንድ አመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የ2 ትሪሊየን ዶላር ጭማሪ አሳይቷል።
የሀገሪቱ እዳ ከጥር እስከ ህዳር 2024 በ6 በመቶ መጨመሩና በአራት ወራት ውስጥ በ1 ትሪሊየን ማደጉንም ዘገባው ጠቅሷል።
የአሜሪካ ግምጃ ቤት የሀገሪቱ ብሄራዊ እዳ ከ35 ትሪሊየን ዶላር ማለፉን ያስታወቀው በሀምሌ ወር እንደነበር ይታወሳል።