የሩሲያ ኃይሎች በምስራቅ ዩክሬን ቩሌዳር የተባለችውን ስትራቴጂካዊ ከተማ መቆጣጠራቸው ተነገረ
የግዛቱ የዩክሬን ባለስልጣን የሩሲያ ኃይሎች ከሁለት አመታት በላይ የሩሲያን ጥቃት ለመቋቋም ስትራቴጂካዊ ምሽግ ወደነበረችው ከተማ መሀል መግባታቸውን ባለፈው ማክሰኞ ተናግረዋል
ከተማዋ በምስራቅ እና በምዕራብ ባሉ የጦር ግንባሮች መገናኛ ላይ የምትገኘው በመሆኗ በሁለቱም ወገን ለሚገኙ ወታደሮች ሎጂስቲክስ ለማድረስ ጠቀሜታ አላት
የሩሲያ ኃይሎች በምስራቅ ዩክሬን ቩሌዳር የተባለችውን ስትራቴጂካዊ ከተማ መቆጣጠራቸው ተነገረ።
የሩሲያ ኃይሎች በምስራቅ ዩክሬን ዶኔስክ ግዛት የምትገኘውን ቩሌዳር ከተማ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠራቸውን ሮይተርስ የሩሲያ የጦርነት ጸኃፊዎችን ጠቅሶ ዘግቧል።
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር የከተማዋን መያዝ እስካሁን አለማረጋገጡን ዘገባው ጠቅሷል።
የግዛቱ የዩክሬን ባለስልጣን የሩሲያ ኃይሎች ከሁለት አመታት በላይ የሩሲያን ጥቃት ለመቋቋም ስትራቴጂካዊ ምሽግ ወደነበረችው ከተማ መሀል መግባታቸውን ባለፈው ማክሰኞ ተናግረዋል።
ሩሲያ ዶኔስክን ጨምሮ አራት የዩክሬን ግዛቷችን የራሷ ሉአላዊ ግዛት አድርጋ የጠቀለለች በ2022 ነበር። ይህ የሩሲያ እርምጃ ዩክሬን እና ምዕራባውያን ሀገራት በጽኑ ተቃውመውታል።
ሞስኮ አጠቃላይ የዶኔስክ ግዛትን ለመቆጣጠር እንደመስፈንጠሪያ ሰለምትፈለረጋት፣ 14ሺ ሰዎች የሚኖሩባትን እና የነዳጅ ከሰል የሚወጣባትን ቩሌዳርን መቆጣጠር ትፈልጋለች።
ከተማዋ በምስራቅ እና በምዕራብ ባሉ የጦር ግንባሮች መገናኛ ላይ የምትገኘው በመሆኗ በሁለቱም ወገን ለሚገኙ ወታደሮች ሎጂስቲክስ ለማድረስ ጠቀሜታ አላት። ቩሌዳር ሩሲያ በ2014 የያዘቻትን ክሬሚያን ከዩክሬን የኢንዱሰትሪ ማዕከል ከሆነው ዶምባስ ግዛት ለሚያገናኘው የባቡር መስመር ቅርብ ርቀት ላይ ትገኛለች።
ከተማዋ በተከታታይ በተደረጉ ውጊያዎች ከፍተኛ ውድመትን አስተናግዳለች።